ምክር ቤቱ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
ምክር ቤቱ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
(ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 4 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 19ኛ መደበኛ ስብሰባው፤የኢትዩጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ፤የሂሳብ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት፤ የሀገር ሃብትን ለመጠበቅና ኢኮኖሚን ለማፋጠን ጠቀሜታው የጎላ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጀ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
ሰብሳቢው አያይዘውም፤ ረቂቅ አዋጁ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባልሙያዎችን ለማፍራት ጥራት ያለው የፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም የሀገርን ኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሂሳብ የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በዘርፉ እየተከሰቱ ያሉ የገንዝብ ብክነትን ለማስቀረት እና የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ሰብሳቢው አስገንዝበዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኢዮብ መኮነን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ተሞክሮዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተቋመው፤ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ እና እንቨንስትመንትን ለማሳለጥ ኢንስቲትዩቱ ሚናው የጎላ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡
ሀገራችን ከፍተኛ ውጪ እያወጣች ከጎረቤት ሀገራት ታሳራ የነበረው የሂሳብ ስራን በሀገር ውጥ ባለሙያዎች ለመተካት አቅም ይፈጥራል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤው ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ኢንቨስትመንት በማሳለጥ በሀገር ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሂሳብ ባለሙያችን በማፍራት በዘርፉ የሥራ ዕድል ጭምር ለመፍጠር ያግዛል ሲሉ የምክር ቤት አባላቱ ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩት ተግባር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተግባር እና ኃላፊነት ጋር ያለው ልዩነት እና አንድነት በግልጽ በአዋጁ መቀመጥ አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ምክር ቤቱ፤የኢትዩጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1372/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በመኩሪያ ፈንታ
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives