አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የስራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ

 (ዜና ፓርላማ) ግንቦት 7 2017 .ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የስራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በአውሮፓ ፓርላማ ምክትል ፕሬዘዳንት ዮኖስ ኦማርጄ የተመራው ቡድን ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር በኢትዮጵያና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

የተከበሩ አቶ ታገሰ የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ቀደም ሲል የነበራቸውን ትብብር በማጠናከር፤ በቀጣይም በዲሞክራሲ ግንባታ፣ በልማት እና በሰላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ ምክትል ፕሬዘዳንት ዮኖስ ኦማርጄ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያነሳች ያለችው የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በአለም አቀፍ ህጎች መሰረት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ምላሽ ያገኝ ዘንድ የአውሮፓ ፓርላማ ፍላጎት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስኬታማ ይሆን ዘንድ የአውሮፓ ፓርላማ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ምክትል ፕሬዘዳንቱ አስረድተዋል፡፡

( አበባው ዮሴፍ)