የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ
የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ
(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ ።
ጠቅላላ ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔና የኮከሱ የበላይ ጠባቂ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እንዳሉት፤ በምክር ቤቱ ጉዳዮች የሥርዓተ-ፆታ ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
ኮከሱ ከምክር ቤታዊ ተልዕኮው ጋር በተጣጣመ መልኩ፤ በሚወጡ ሕጎች፣ በሚያደርጋቸው የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች፣ በሕዝብ ውክልናና በፓርላማ ዲኘሎማሲ ሥራዎች የስርዓተ ጾታ ተካታችነት በአግባቡ ምላሽ እንዱያገኝ ለማስቻል የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባር መከናወኑን ገልፀዋል።
ኮከሱ የ4 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱን የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ አስታውሰው፤ ባለፉት 3 ዓመት ተኩል ከዕቅዱ አንፃር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማና አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተለይ ጾታዊ እኩልነት እና ሴቶች በሁለም የልማት መስኮች ፍሕታዊ ተሳታፊነታቸውና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ኮከሱ የበኩሉን ሚና ሲወጣ መቆየቱንም አብራርተዋል።
በሴቶችና ህጻናት ሊይ በሚደርሱ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዲዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በምክር ቤቱ ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት እና ከሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ስለመሥራቱ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ አብራርተዋል።
ኮከሱ ተልዕኮውን በአግባቡ ለመወጣት ከሚያስችሉት ጉዳዮች መካከል የአመራሩንና የአባላቱን አቅም መገንባት ቁልፍ ተግባሩ መሆኑን የገለፁት የኮከሱ የበላይ ጠባቂ፤ በተለያዩ ዘርፎች የአባላቱን ፍላጎትና ክፍተቶችን ያገናዘበ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡
ኮከሱ በተፈጥሮና በሰውሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከአጋር አካላት ድጋፍ በማሰባሰብ በዓይነትና በገንዘብ የሰብዓዊ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ የተደረገው ድጋፍ ፍትሃዊነቱንና ተገቢነቱን የማረጋገጥ ሥራም መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
ኮከሱ ከአቅም ግንባታ፣ የሥርዓተ-ፆታ ጉዲይ ተካታችነትን ከማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ከማድረግ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጠናከር፣ የመረጃ ተደራሽነትና የልምድ ልውውጥ ሥራዎችን ከማስፋት አንፃር ውጤታማና አመርቂ ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል፡፡
በኮከሱ 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኮከሱ የ3 አመት ተኩል የዕቅድ አፈፃፀም በኮከሱ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ኪሚያ ጂንዲ የቀረበ ሲሆን፤ የኮከሱን የ3 አመት ተኩል አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት በኮከሱ የስራ አስፈፃሚ አባል በተከበሩ ወ/ሮ አስቴር ከፍታው ቀርቧል፡፡
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives