2018 የፌዴራል መንግስት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ

 (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 26 2017 .ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 42 መደበኛ ስብሰባው፤ 2018 የፌዴራል መንግስት በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ 2018 ረቂቅ በጀት ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ግብን ለማሳካት በጀትን በቁጠባና በውጤታማነት ለመጠቀም ታሳቦ የተዘጋጀ ረቂቅ በጀት መሆኑን የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢው አያይዘውም ከጠቅላይ በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር ለመደበኛ 1.2 ትሪሊዮን ብር ሲሆን ለካፒታል ደግሞ 415.2 ቢሊዮን ብር የተበጀተ መሆኑን  ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

2018 በጀት፤ ከባለፈው ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ጋር ሲነፃፀር 34.4 መቶ ዕድገት ማሳየቱን ሰብሳቢው አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በጀት ዓመቱ የውጪ አሸፋፈን በተመለከተ የሀገር ውስጥ ገቢ 1.1 ትሪሊዮን ብር፤ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 129 ቢሊየን ብር እና ከልማት አጋር ድርጅቶች 236 ቢሊዮብ ብር እንዲሁም  ከፕሮጀክቶች እርዳታ 47 ቢሊዮን ብር ለማግኘት እንደታቀደና የሀገር ውስጥ የውጭ ዕርዳታ ገቢ 81 በመቶው እንደሚሽፍን የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ አብራርተዋል፡፡

በጀቱ የሀገርን ዕድገት የሚያሳይ እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ የምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት ለታለመለት ዓለማ በቁጠባና በላቀ ውጤታማነት ስራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው የምክር ቤት አባላት አስገንዝበዋል፡፡

እንዲሁም የሀገርን የውስጥ የገቢ አቅም በማሳደግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል በጀትን በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የፌዴራል መንግስት 2018 ረቂቅ በጀት አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1390/2017 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል፡፡