"ልዩነቶችን በማጥበብ ለሀገር ዕድገት በጋራ መስራት ይገባል"

      --  የተከበሩ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ---

(ዜና ፓርላማ) ሚያዚያ 22 ቀን፣ 2017 .ም፤ አዲስ አበባ፤ ‹‹ልዩነቶችን በማጥበብ ለሀገር ዕድገትና ጥቅም በጋራ መስራት ይገባል›› ሲሉ የሕዝብ የወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡

ተቋማት አቅደው ለጋራ ሀገራዊ ዕድገት ለውጤት መስራት እንደሚገባ የተከበሩ ምክትል አፈ ጉባኤዋ ጠቁመው፤ የለውጡ መንግስት ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ እየተጋ እና እየሰራ ያለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተቋማት ወቅቱ የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎትን አዳብረው በመስራት ሁሉም ለሀገሩ ጥቅም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅበት የተከከበሩ  ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አስገንዝበዋል፡፡

የተፎካካሪ ፓርቲዎችም ለጋራ የሀገር ጥቅም በአንድነት እና በትብብር መስራት ለውጦችን መቀበል በሚዛናዊነት ማየት እና መረዳት እንደሚገባ የተከበሩ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አሳስበዋል፡፡

የውጭ ጠላቶች የውስጥ ግጭቶችን  እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሀገር ሉአላዊነት እና ዕድገት ተፅእኖ እንዳያሳድሩ መንግስት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እና የዲፖሎማሲ ሥራ መስራት እንዳለበት የተፎካካሪ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት አስገንዝበዋል፡፡

የቀረበው ሰነድ  ሀገራዊ ጉዳዮችን በጋር ለመፍታት አቅም የሚፈጥር መሆኑን የተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡