"ምክር ቤቱ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን አከናውኗል " የተከበሩ / ሎሚ በዶ 

(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 30 ቀን፣ 2017 .ም፤ አዲስ አበባ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ / ሎሚ በዶ ምክር ቤቱ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን አከናውኗል ሲሉ ገለፁ፡፡

የምክር ቤቱን 2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርትን 3 ልዩ ሰብሰባው አድምጧል፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ / ሎሚ በዶ ተቋሙ በሕገመንግስቱ እና በህዝብ ዘንድ የተሰጠው ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የዕቅድ ዓላማውን ለማሳካት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በፓርላማ ዲኘሎማሲ በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ፣ የሀገራትን ግንኙነትን ለማጠናከር፣ የልምድ ልውውጥ በማድረግ፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለመሣብና ለማሳለጥ፣ በዲሞክራሲ፣ በጤናውና ትምህርት ዘርፉ መደጋገፍን ማጠናከር መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በዲፕሎማሲው በተሰራው ሥራ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትና ራስን ለመቻልና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተሠሩ ያሉ ሥራዎች በጥናት ተሰንዶ መረጃን ለምስራቅ አፍሪካ የግብርና ተቋማት ማቅረብ መቻሉን የተከበሩ / ሎሚ በዶ ገልጸዋል፡፡

ዲፕሎማሲ ስራዎችን ለማጠናከር ያግዝ ዘንድ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ዘርፍ ለምክር ቤት አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን የተከበሩ / ሎሚ በዶ ጠቁመዋል፡፡

ለሀገር ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ዲፕሎማሲ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በርካታ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ማከናወን መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡