"በኢትዮጵያ ፍትሕ እና ርትዕ እንዲረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል

---- የተከበሩ / ሎሚ በዶ

(ዜና ፓርላማ) ሚያዝያ 25 2017 .ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ / ሎሚ በዶ በኢትዮጵያ ፍትሕ እና ርትዕ እንዲረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ  ይገባል ሲሉ አስገንዘቡ።

የተከበሩ / ሎሚ ይህን ያሉት አገራዊ የፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታና የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።

ምክር ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት በሚያከናውናቸው የሕዝብ ውክልና እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች የፍትሕ ጉዳይ ዋነኛ የኀብረተሰቡ ጥያቄ ስለመሆኑ ምክትል አፈ ጉባኤዎ ጠቁመዋል።

ለዚህም በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ተቋማት እንዲሁም ምክር ቤቶች የሕዝቡ የፍትሕ ጥያቄ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ በትኩረት እና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በኦሮሚያ ክልል የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑንም አመላክተዋል።

በክልሉ የፍትሕ አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ፈጣን እንዲሆን የአመራርና ፈፃሚ አካላት የተናበበና የተቀናጀ ድምር ውጤት  በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በየደረጃው ባሉ ችሎቶች እንዳሉ መገንዘብ የሚቻል መሆኑን የተከበሩ / ሎሚ በዚሁ ጊዜ ገልጸዋል።

በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሁም በዞንና ባህላዊ ፍርድ ቤቶች በአመራርና በፈፃሚዎች ቅንጅት የተመዘገበው ውጤት በሌሎች ክልሎችም ማስፋፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።