ኢትዮጵያ 6.1 በመቶ  የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡

(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 14 ቀን 2013 .ም፤ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኮኖሚያዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በማስጠት ላይ ናቸው፡፡

የኑሮ ውድነትን ጨምሮ ለተነሱት የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የብድር ጫና መቀነስ፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ፣ ኤክስፖርትን እና ገቢን የማሻሻል ዋናዋና ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም በግጭት ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መውደሙን ጠቁመው ይህም ሆኖ ባለፈው ዓመት አገሪቱ 6.1 በመቶ እድገት ማስመዝገቧን እና ከሌሎች አገሮች አንጻር ሲታይ ቀዳሚ መሆኗን አብራተዋል፡፡ ብዙ የሕዝብ ቁጥር ላላቸው አገሮች አጠቃለይ እድገቱ በነብስ ወከፍ ገቢ ላይ ቶሎ ለውጥ የማያሳይ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በአገሪቱ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት የአገሪቱን ኢኮኖሚ የበለጠ የሚያነቃቁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የዋጋ ንረትን በተመለከተ የእርሻ ግብዓት የሆነው ማዳበሪያ 30 በመቶ ጭማሪ ማስመስገቡ፣ አለማቀፍ ጫናዎች እንዲሁም ስግብግብ ነጋዴዎች ንረቱን እንዳባባሱት ነው ያብራሩት፡፡

መንግስት እነዚህን ችግሮች ለማፍታት በአገር ውስጥ ስንዴን የማምረት፣ የዳቦ አቅርቦትን የማሳደግ፣ የግብይይት ስርዓቱን የማሻሻል፣በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሳድ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡