(ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 13፣ 2015 ዓ.ም፤ ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገው 6ኛ ዙር 2ተኛ ዓመት 1ኛ ልዩ ስብሳባው ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ለማንሳት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የውሳኔ ቁጥር 12/2015 ሆኖ በ61 ተቃውሞ፣ በ5 ድምፀ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡

በህወሐትና በፌደራል መንግስት በኘሪቶሪያ የተደረገውን ሥምምነት ለማጽናት፤ ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተነስቷል፡፡

የሀገሪቱን ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓት ባከበረና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ በፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት መሠረት በማድረግ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት እንዲቻል ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት አስፈላጊ አንደሆነ የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ