ጥቆማ ለም/ቤቱ ስለሚቀርብበት ሁኔታ

ራዕይ፣ ተልዕኮ ፣ እሴቶች

  • ራዕይ

    በ2015 የዳበረ የመድበለ ፓርቲ ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ ተቋም በመገንባት በአፍሪካ ተምሣሌት መሆን.

  • ተልዕኮ

    1 - ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ ለመልካም አስተዳደርና ሰላም መስፈን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መረጋገጥ የሚረዱ ሕጐችን ማውጣት፣

    2 - በም/ቤቱ ለወጡ ሕጐች፣ ለፖሊሲዎችና እቅዶች ማስፈጸሚያ የተመደበ ሐብት በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ መዋሉን በመከታተልና በመቆጣጠር የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣

    3 - በም/ቤቱ የመድበለ ፓርቲ ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ የሚጐለብትበትን አሠራርና ሥርዓት መዘርጋት፣ በም/ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የሆነ ተሳትፎ መኖሩን ማረጋገጥ፡፡

  • እሴቶች

    1 - ለሕገመንግሥቱና ለሕዝብ ተገዥ መሆን፣

    2 -የሕግ የበላየነትን ማክበር፣

    3 - መቻቻልና የጋር መግባባት፣

    4 -ግልጽነት፣ ቅንነት፣ አሳታፊነትና ተጠያቂነት

    5 - ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ አሠራርን መከተል

  • አድራሻ

    ስልክ: +251-111-241000

    ፋክስ: +251-111241004

    የፖ.ሣ. ቁጥር: 800001

    ኢ-ሜይል: info@hopr.gov.et

አድራሻ

አድራሻ: 

የስልክ ቁጥር: +251-111-241000

ፋክስ: +251-111241004

የፖ.ሣ. ቁጥር:

የምክር ቤቱ ሥልጣን፣ ተግባር እና አደረጃጀት

1/ MKR b¤tÜ bÞgmNGotÜ xNqI 55 XNÄþhùM bxNqI 70 (1)

የኢትዮዽያ ፓርላማ ታሪክ

null History of Ethiopian Parliament

የቀዳማዊ  ኃይለሥላሴ  የመጀመሪያው ሕገ መንግስት  ከታወጀበት  ሐምሌ  9  ቀን  1923 ዓ.ም በኋላ ጥቅምት 24 ቀን 1924ዓ.ም የመጀመሪያው ፓርላማ መከፈቱን የታሪክ ድርሳናት ያሰረዳሉ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የፓርላማ ስርዓት በኢትዮዽያ  ሲሰራበት የቆየ  ሲሆን፤መገለጫዎቹ እንደ የመንግስታቱ ባህሪያ   የተለያዩ ናቸው። በሶስት መንግስታት ዘመን የፓርላማ ስርዓት አተገባበር ምን እንደሚመስል  በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ፓርላማ  በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት( ዘውዳዊ ስርዓት ፤ከ1923 እስከ 1967 .)
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፅሁፍ ሕገ-መንግስት የወጣው በቀዳማዊ  ኃይለሥላሴ  ዘመነ መንግስት  በ1923 ዓ.ም  ሲሆን፤ የንጉሠ ነገሥቱ የንግስ በዓል  ጥቅምት 23 ቀን 1923 .ም  ከተከበረ በኋላ፤ ሐምሌ 9 ቀን 1923 ዓ.ም.  ንጉሱ በፊርማቸው ሕገ መንግስቱን  አፅድቀው፤ በፍቃዳቸው ለኢትዮዽያ ህዝብ የሰጡት የመጀመሪያው  ሕገ  መንግስት  በመባል ይታወቃል።

ይህ ሕገ መንግስት  ያስፈለገበት  ምክንያት ኢትዮዽያ ከነበረችበት ጥንታዊና ልማዳዊ አመራር ወጥታ ወደ ዘመናዊ አስተዳደር እንድትሻገር ብሎም ኢትዮዽያ በህገ መንግስት የምትተዳደር ንጉሳዊ አገር ነች ተብላ በዓለም እንድትታወቅ ለማድረግ ነው። ከታላላቅ መሳፍንትና መኳንንት ወገን 11 የኮሚቴ አባላት በንጉሱ ተመርጠው በራስ ካሳ ሊቀመንበርነት በየዕለቱ እየተሰበሰቡ በአምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተመስርተው በሕገ መንግስቱ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ጥናት ካደረጉ በኋላ ፤ የሕገ መንግስቱ ረቂቅ ተዘጋጅቷል።

1. የንጉሠ ነገሥቱ ዘውድ  አወራረስ  ከሣህለሥላሴ እና ቀ.ኃ.ሥ የትውልድ መስመር ሳይወጣ ከልጅ ወደ ልጅ እንዲተላለፍ የሚወስን፣

2.  የኢትዮዽያን ሕዝብና የግዛት አንድነት የሚያረጋግጥ፣

3.  የማዕከላዊውን የንጉሠ ነገሥት መንግስት ሥልጣን የሚያጠናክር፣

4. የንጉሠ ነገሥቱ መንግስት እስካሁን በልማድ ሲጠቀምበት ከኖረው ፍፁም ፌዎዳላዊ አመራር ወደ ባለሙሉ ስልጣን ዘውዳዊ አስተዳደር ተሻጋግሮ በተወሰነ ደረጃ በሕዝብ ምክር ቤት አስተያየት እየታገዘ የሚሰራ፣

5. ፓርላማው የሕዝብን መብትና ግዴታ የሚመለከቱትን መሰረታዊ ጉዳዮች እያጠና በሕግ እንዲደነገጉ ለንጉሠ ነገሥቱ ሃሳብ ለማቅረብ እንዲችል ፤ አምስቱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።

ሕገ መንግስቱ ለአገሩም ሆነ ለህዝብ የሚሰጠው ጥቅም  ምን እንደሆነ ለመሳፍንቱና መኳንንቱ አስረድቶ ለማሳመን ንጉሱ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም፤ በሕገ መንግስቱ ረቂቅ ላይ ሕዝብ እንዲወያይበት አልተደረገም ነበር። በሕገ መንግስቱ ከአንቀፅ 18 እስከ 28 ድረስ የህዝብ መብቶች የተደነገጉ ቢሆንም፤ ለዘውዳዊ ስርዓት መጠናከር ሕጋዊ ዋስትና ያስገኘ  ሕገ መንግስት መሆኑ  በበርካታ አንቀፆቹ  ሰፍሮ ይገኛል። ለአብነት ያህል  አንቀፅ 2፤  “የኢትዮዽያ መሬትም፣ሕዝቡም፣  ሕጉም  በጠቅላላው የንጉሠ ነገሥት ነው"  የሚል  ይገኝበታል።

ፓርላማው የንጉሠ ነገሥቱ  መንግስት አማካሪዎች የሆኑትን  የሕግ መወሰኛንና የሕግ መምሪያ  ምክር ቤቶችን የያዘ ተቋም ነው።

የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አማካሪዎች( በዘመናዊ አጠራር ሴናተሮች) ቀጥታ በንጉሠ ነገሥቱ የሚመረጡ ናቸው። የሚመረጡትም ከመሳፍንትና ከመኳንንት ወገን  የሆኑ ጠቅላይ ገዥዎችና  የታወቁ ባላባቶች   እንዲሁም   በሚኒስትርነት፣ በዳኝነት፣ በጦር አለቅነት፣  መንግስታቸውን ለብዙ ዘመናት ካገለገሉት መካከል ነው። የሕግ መወሰኛ አባላት ኃላፊነት የንጉሠ ነገሥቱ መንግስት ለአገር ስለጣኔና ልማት የሚያዘጋጃቸውን ሕጎችና ደንቦች ፣ከታላላቅ የውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርጋቸውን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስምምነቶች መርምሮ አስተያየት መስጠትና ማፅደቅ ነው።

የሕግ  መምሪያው ምክር ቤት አማካሪዎችን(የሕዝብ እንደራሴዎች) ሕዝቡ ራሱ በቀጥታ ለመምረጥ ችሎታው እስኪፈቅድለት እስከ ተወሰነ ዘመን ድረስ በአካባቢው  ባላባቶች እንዲመርጡ  የ1923ቱ ህገ መንግስት ይደነግጋል። መንግስት በሕዝቡ ስም የሚመርጣቸው እነዚህ አማካሪዎች ለቅርፅና ለወግ ካልሆነ በስተቀር የሕዝብ ተወካዮች ነን ብለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ  የሚችሉ አልነበሩም። መንግስት አስተያየት እንዲሰጡበት የሚጠይቃቸውን ተቀብለው ከመምከር በስተቀር እርመጃ መስደው  አስተዳደሩን መተቸትም ሆነ መቆጣጠር አይችሉም ነበር፤ በተለይም የንጉሠ ነገሥቱን ሚኒስትሮች ለአስረጅነት ወደ ፓርላማ እንዲመጡ መጥራት አይፈቀድላቸውም። ስለሆነም ዘመናዊ የፓርላማ አሰራርን ያልተከተለ፤ ምንም ዓይነት ስልጣን የሌለው ፓርላማ ነበር ማለት ይቻላል።

በ1948 ዓ.ም  ሕገ መንግስቱ ሲሻሻል የሕግ መምሪያ  ምክር ቤት አባላት በቀጥታ ህዝብ   እንዲመርጥ  ተደርጓል።  በዚህም መሰረት 125 የሕግ መምሪያ እና  250 የህግ መወሰኛ ምክርቤተ አባላት ተመርጠው፤ፓርላማው ንጉሱን ከማማከር ወደ ሕግ አውጪነት  ስልጣን  መሸጋገር የቻለ ሲሆን፤ ቋሚ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ጉዳዮችን እንዲያጣሩና የውሳኔ  ሃሳብ  ለምክር ቤቱ  እንዲያቀርቡ ተደርጓል

ሆኖም በ1948 ሕገ መንግስት በቀጥታ በሕዝብ ምርጫ የተፈጠረው የብሔራዊ ሸንጎው የሕግ መምሪያ ምክር ቤት፤በዜግነት መብት ብቻ ሳይሆን በሃብት ሚዛን የተመረጡ የገጠር ጉልተኞችና የከተማ ከበርቴዎች መሰብሰቢያ በመሆኑ፤ ለሕዝብ ጥቅም ቆሞ የአፄውን ፍፁም ስልጣንና የፌዎዳል ስርዓቱን የሚቃወም የፖለቲካ አካልና መድረክ ሊሆን አልቻለም።

 ሕገ-መንግስቱ  እንደገና የተሻሻለ ቢሆንም በ1966 ዓ.ም በወርሃ ይካቲት ህዝባዊ አመፅ በመቀስቀሱ ፤ሳይታወጅ  ህዝባዊ አብዮት ፈንድቶ፤ ንጉሠ ነገሥቱም  መስከረም 2 ቀን 1967 . በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከሥልጣናቸው ወረዱ። ወደ ሥልጣን የመጣው ወታደራዊው ቡድን ደርግ ፓርላማውን በተኖ፤ አገሪቱ የሶሻሊዝም ርዕዮተ አለም እንደምትከተልአወጀ።    

 የደርግ  ብሔራዊ ሸንጎ  (  ወታደራዊ ስርዓት ፤1980 እስከ 1983 .)

ደርግ  ማለት ኮሚቴ ሲሆን አባላቱም ከሻለቃ በታችና የባለሌላ ማዕረግ  ማርክሲስታዊ  መኮንኖች  ናቸው። ደርግ ራሱን ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ብሎ በማወጅ ፤የፖለቲካ ስልጣን ከያዘበት  ከመስከረም 2ቀን 1967 ዓ.ም  እስከ መስከረም 1980 . ድረስ  ለ13 ዓመታት  ያለ ሕገ-መንግስት አገሪቱን  መርቷል ።

ጊዜያዊ  ወታደራዊ  መንግስት ደርግ እራሱን ወደ  ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲን/ ኢሰፓ/   አደራጅቶ፤የኢህዲሪ ሕገ-መንግስትን  መስከረም 2 ቀን 1980 . አፅድቋልብሔራዊ ሸንጎውን በመቆጣጠር  በአንድ ፓርቲ ስርዓት አገሪቱን   መርቷል ። የብሔራዊ ሸንጎው የሥራ ዘመን  አምስት  ዓመት  ሲሆን፤ አባላቱም  835 ምርጫ ክልሎች  የሚመረጡ ናቸው ሸንጎው በዓመት አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ ሆኖ፤ የመንግስት ምክር ቤት በሸንጎው የሚወሰኑ ጉዳዮችን እንደሚያመቻች ሕገ-መንግስቱ  ይደነግጋል። 

የሽግግር መንግስት (ሰኔ 1983 . እስከ ሐምሌ 1987ዓ.ም)
ኢህአዴግ  የደርግን መንግስት በትጥቅና ፖለቲካ ትግል   ከሥልጣን  አስወግዶ አገሪቱን በተቆጣጠር ማግስት  የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች  ጥሪደርጎላቸው የሰላምና የዴሞክራሲ ኮንፈረንስ ከሰኔ 24—28/1983 ዓ.ም በአዱስ አበባ  ከተካሄደ በኋላ  የሽግግር መንግስት ቻርተር  ፀድቋል። ይህ ቻርተር የተወካዮች ምክር ቤት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤትን አቋቁሟል። የአገሪቱ ሕግ አውጪ አካል የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት  አባላቱ ከተለያዩ ፖለቲካ ዴርጅቶች፣ ንቅናቄዎች እና ግንባሮች የተወጣጡ 86 አባላት ያሉት ሲሆን
3 ሴቶች ነበሩ። የቻርተሩ ይዘትና ተልዕኮ ያለፈው መንግስት የመጨቆኛ ተቋማትበሙሉ ማፈራረስ፣በህዝባዊ መንግስት አማካኝነት የተገፉ ዜጎችን መብትና ጥቅም ማስከበር፣አካባቢያዊ አድሎዎችን ማካካስና ማስቀረት እንዲሁም የሽግግር ፕሮግራሞችን ማሳካት የሚሉ ይገኙበታል

ምክር ቤቱ አራት ዓመታት የቆየ ሲሆን ዋና ሥራውም ቋሚ መንግስት የሚመሰረትበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነበር። በዚህም መሠረት የሕገ-መንግስት ኮሚሽን ተቋቁሞና በኮሚሽኑ አማካይነት የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት  ረቂቅ ከተዘጋጀ በኋላ በህዝብ አስተያየት ዳብሮ   ህዳር 29 ቀን 1987 . ፀድቋል።

በዚህ ሕገ-መንግስት መሠረትም ግንቦት 1987 .ም ብሔራዊ ምርጫ ተካሄዶየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመሰረተ፤ ምክር ቤቱ ነሐሴ አጋማሽ ላይ ባደረገው ስብሰባ የሽግግር መንግስቱ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ክቡር አቶ መለስ ዜናዊን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፤ የፖለቲካ ስልጣን በህዝብ ለተመረጠ መንግስት በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ  በሆነ መንገድ ተሸጋግሮ የሽግግር መንግስቱ የስልጣን ዘመን ፍፃሜ ሆነ፡፡


የኢፌዲሪ መንግስት ፓርላማ(ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፤ከ1987 ዓ.ም.------)

በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ   53  መሰረት የፌደራሉ መንግስት ሁለት ምክር ቤቶች ይኖሩታል፤ እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ናቸው። በዚህም መሰረት ከነሐሴ 1987 . ጀምሮ እነዚህ ምክር ቤቶች ተቋቁመዋል።

የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራሉ መንግስት ከፍተኛ የስልጣን አካል ሲሆን፤ አባላቱም   ሁሉ አቀፍ፣ ነፃ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምፅ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ  በሚካሄድ  ምርጫ በህዝብ  ይመረጣሉ።የምክር ቤቱ አባላት በአንድ ምርጫ  ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምፅ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ስርዓት ይመረጣሉ።የተለየ ውክልና ያስፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በምርጫ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይሆናሉ።

የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የህዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ 550 የማይበልጥ ሆኖ፤ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሔረሰቦች 20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስቱአንቀጽ 50(3) ድንጋጌ መሰረት ተጠሪነቱ ለሀገሪቱ ህዝብ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55 እንዲሁም በአንቀፅ 70(1)፣ አንቀፅ 79 (4) (ሐ)፣ አንቀፅ 82 (2)   (ሐ)፣አንቀፅ 101፣ አንቀፅ 102፣ አምቀፅ 103 እና 104  የተዘረዘሩት ሥልጣንና ተግባራት ያሉት ሲሆን፤ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው:-

  • ሕግ ማውጣት፣
  • የፌደራል መንግስት በጀትን መርምሮ ማፅደቅ፣
  • መንግስታዊ አካላትን መከታተል፤ መቆጣጠር እና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝም እርምጃ መውሰድ፣
  • የራሱን የተለያዩ ኮሚቴዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ክፍሎችን ማቋቋምና ማደራጀት፣
  • በራሱ የሚሰየሙ፣ የሚሾሙ እና የሚመረጡ የመንግስት ባለስልጣናትን መሰየም፣መሾም፣ማፅደቅና መምረጥ፣
  • አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር እንዲገናኙ  ማመቻቸት።