null የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያከናውናል፡-

ሀ/ የፌደራል መንግሥቱ የፍትህ አስተዳደር ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ መደራጀቱንና በአግባቡ ተግባሩን እያከናወነ መሆኑን፤

 ለ/ በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉ መብቶችና ነፃነቶች በአግባቡ መተግበራቸውን፤

ሐ/  ነፃና ፍትሃዊ የምርጫ ስርዓት መዘርጋቱን እና ሂደቱን፤

መ/ ሕብረተሰቡ ነፃ፣ ፍትሃዊና ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ማግኘቱን፤

ሠ/ ሙስናና ብልሹ አሠራርን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት በአግባቡ መዘርጋቱንና ሥራ ላይ መዋሉን፤

ረ/ በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 54 (6) የተመለከተውን የህግ ከለላ የማንሳት እንዲሁም ሌሎች የአባላት መብትና ሥነ-ምግባር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፤

ሰ/ የወንጀል መከላከል ስራ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን እንደዚሁም ለወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች በቂ ጥበቃ መደረጉን

ሸ/ የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል የህግ ምክር፣ ክስና ክርክር እየተካሄደ መሆኑን፤

ቀ/ በየደረጃው የሚገኙ የፌደራል መንግስት የዳኝነት አካላት በሕግ የተሰጣቸውን ተግባር እና ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን፤

በ/ የመገናኛ Bzù¦N lxg¶ Ä!äK‰s!ÃêE |R›T GNƬ½ s§M L¥T ybk#§cWN ¸Â XytÅwtÜ mçnùN

ተ/ የmNG|T mg¾ Bz#¦N ïRìC ytÈlÆcWN ¦§ðnT bxGÆb# መወጣታቸውን፤

ቸ/ የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣  ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸውን ፤

ኅ/ የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማት የተመደበ ላቸውን በጀት በአግባቡና በውጤታማነት በስራ ላይ ማዋላቸውን

 2/ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምክር ቤቱ ወደ ማንኛውም ቋሚ ኮሚቴ የሚመራውን ረቂቅ ህግ እና የሚቀርቡ የረቂቅ ህጎችን የረቂቅ ህግ አዘገጃጀት መርሆዎችን የተከተሉና የተሟሉ መሆናቸውን ይመረምራል፡፡

ተ.ቁ

የተቋሙ ስም

1

የፍትህ ሚኒስቴር እና ተጠሪ የሚደረጉለት ተቋማት፣

2

ከአስፈፃሚ አካላት ውጪ ያሉ የዲሞክራሲ ተቋማት፣

3

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት፣

የኮሚቴ አባላት