null የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያከናውናል፡-

  1. የሀገር ውስጥና የውጭ ንግድን የሚመለከቱ ቀጣናዊ በተለይም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖር የንግድና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ፣ ሀገራዊ የጥራት መሰረተ ልማቶችን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ህጎችን መውጣታቸውን፣ አፈጻጸሙ ከሀገራዊ የልማት አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ ዝርዝር መርሀ ግብር መዘጋጀቱን፤
  2. የሀገር ውስጥ ንግድ እንዲስፋፋና እንዲዘምን፣ ሕጋዊ አሠራር እንዲሰፍን ተገቢነት ያላቸውን እርምጃዎች መወሰዳቸውን፤
  3. የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ድጋፍ የሚሰጥበትን ሥርዓት መዘርጋቱን፣
  4. የንግድ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት በሚያፋጥን መልኩ ተግባራዊ መሆኑን፤
  5. የአገር ውስጥ ንግድ እንዲስፋፋ እና ህጋዊ የንግድ አሠራር እንዲሠፍን የሚያስችሉ እና የሚያበረታቱ ተግባራት በአግባቡ መከናወናቸውን፤
  6. የውጪ ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁኔታዎች  መመቻቸታቸውን፤
  7. ከወጪና ገቢ እቃዎች ጋር የተያያዙ ችግሮችን እንደዚሁም ፀረ-ውድድር የንግድ ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስርዓቶች መዘርጋታቸው፤
  8. ለሸማቾች አስፈላጊው ጥበቃ መደረጉን፤
  9. የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት እና የንግድ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ማበረታቻ፤
  10. የንግድ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያሳድጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መዘጋጀታቸውን፤
  11. የውጭ ንግድ የሚስፋፋበትና የሚጠናከርበት ስትራቴጂ መቀየሱን፤
  12.  የቱሪዝም ልማትና ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን ስትራቴጂዎችን የህግ ማዕቀፎችን መቀረጹን ከሀገራዊ የልማት አቅጣጫ ጋር መጣጣማቸውን እና አፈጻጸማቸውን፣
  13. በቱሪዝም ዘርፍ ልማት የግል ዘርፉን ተሳትፎና ሚና ለማሳደግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱን እና ተግባራዊ አፈጻጸሙን፣
  14. የቱሪዝም መዳረሻዎችን መሠረተ ልማት መጠናከራቸውንና አዳዲስ መሠረተ ልማቶች መገንባታቸውን፣
  15. የቱሪዝም መረጃዎች በአግባቡ መሰብሰባቸው መደራጀታቸው እና መሰራጨታቸው
  16. የአገሪቱን የተፈጥሮ ቅርሶች በአግባቡ እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው መልማታቸውና ጥቅም ላይ መዋላውን፣
  17. በፌደራል መንግስት እንዲተዳደሩ የተሰየሙ የዱር እንስሳ ጥበቃ ቦታዎች በአግባቡ መጠበቃቸውና ስትራቴጂዎችና ኘሮግራሞች መቀረፃቸውን፣
  18. ለአገሪቱ yt$¶ZM MNunT y¸ÃglGl# xSf§g! h#n@¬ãC mmÒc¬cWN እና የቱሪዝም መስህቦችና መልካም ገፅታዎች መተዋወቃቸውን፤
  19. የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማት የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣  ስትራቴጂዎች  እና  ዕቅዶች  በአግባቡ  በሥራ  ላይ  መዋላቸውን
  20. የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣  ስትራቴጂዎች እና እቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸውን፤
  1. የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡና በውጤታማነት በስራ ላይ ማዋላቸውን፡፡

የኮሚቴ አባላት