null Gov't Whip

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ጽ/ቤት እንደ አብዛኛው ፓርላመንታዊ ስርዓት ተከታይ ሀገሮች በኢትዮጲያም ምርጫ ያሸነፈው ፓርቲ የመሰረተው መንግስት ጠቅላይ ሚንስትር የሚሰይሟቸው ተጠሪዎችን የሚያቅፍ ጽ/ቤት ነው። በ2014 ዓ.ም በተካሄደው ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፎ መንግስት የመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስቴር (Chief Government Whip) ሲኖረው ሁለት ምክትል የመንግስት ተጠሪዎች በሚንስቴር ዴኤታ ማዕረግ አሉት። የመንግስት ተጠሪ በዋናነት ፓርቲው በእጩነት አቅርቧቸው ህዝብ አምኖ ለመረጣቸው የህዝብ ተወካዮች ድጋፍ የሚሰጥና ክትትል የሚያደርግ ተቋም ነው።