መንግስት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ
(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ መንግስት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በኮደር ልማት፣ በማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሊደር ልማት አሁን ላይ በበርካታ የክልል ከተሞች መስፋፋቱን እና ውጤታማ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተሰራው ኮሊደር ልማት ከተማዋን ከማስዋብና ባለፈ ለነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች በሀገራቸው ጥሩ መዝናኛ ስፍራ እንዲያገኙ ዕድል የፈጠረላቸው መሆኑንም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይም በኮሊደር ልማት የተነሱ ዜጎችም ፍትሐዊ እና ለኑሮ አመቺ የሆነ አካባቢ እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተም በበጀት አመቱ ሶስት ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የስራ ዕድል እንዲያገኙ መደረጉንም አመላከተዋል፡፡
መንግስት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰራ ነው ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ህብረተሰቡ በመንግስት የሚሰሩትን መሰረተ ልማቶች የራሱ መሆናቸውን በአግባቡ ተግዝቦ ሊጠብቃቸውና ሊንከባከባቸው እንደሚገባም አሳስሰበዋል፡፡
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives