(ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 26፣ 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 13ኛው መደበኛ ጉባዔው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመትን መርምሮ አፅድቋል።

የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ክቡር አቶ ተስፋዬ በልጂጌ ሲሆኑ፤ ሹመቱ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81 (2) መሰረት መቅረቡን አብራርተዋል።

የተሿሚዋን የከብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የትምህርት እና የስራ ልምድንም ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የምክር ቤት አባላትም ተሿሚዋ ባላቸው የትምህርትና የስራ ልምድ ለቦታው ብቁ ናቸው ሲሉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በውሳኔ ቁጥር 14 እና 15/2015 ዓ.ም. በ2 ድምጸ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ወ/ሮ ዛህራ ኡመር አሊ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሀላም ፈጽመዋል።

በ ኃይለሚካኤል አረጋኸኝ

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ