(ዜና ፓርላማ)፤ መስከረም 10፣ 2015 ዓ.ም.፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በከተማዋ ነዋሪዎች የሚነሱ የልማትና የጸጥታ ጥያቄዎች በሚፈቱበት ሁኔታ ተወያይተዋል።

ነዋሪዎቹ የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ የድጎማ ስርዓት በመዘርጋት በእሁድ ገበያ በማስፋፋት ሸማችና አምራችን የማገናኘት፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች እና ተማሪዎችን የምገባ መርሃ ግብር ማድረጉ የሚደነቅ ቢሆንም መሠረታዊ የሸቀጦች ዋጋ ንረት እንዲረጋጋ ለማድረግ ተጨማሪ ተግባራት እንዲከናወኑ ጠይቀዋል።

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና የወጣቶች የስራ አጥነትንም ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ ነዋሪዎቹ አሳስበዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው የከተማው አስተዳደር የህብረተሰቡን ህይወት ለመለወጥና ከተማዋን ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልፀው የነዋሪውን የእለት ተእለት ኑሮ እየተፈታተነ ያለውን ኑሮ ውድነት ለመቅረፍና ከተማዋን ምቹ ለማድረግ የከተማው አስተዳደር የበለጠ አቅዶ መሥራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በከተማው በተካሄዱት ውይይቶች የየሴክተር ኃላፊዎች በህብረተሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎች ወቅታዊ ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክረው ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ