(ዜና ፓርላማ)፤ መስከረም 11፣ 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በውይይቱ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ- ጉባዔን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የየተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ በፍትህ ዙሪያ ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ስለዚህም በፍትህ ዘርፍ ባሉ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር ውጤታማ ሥራ ሊሠራ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በአሠራር ሥርዓት ዝርጋታና በግንኙነት አግባብ ከተሣታፊዎች በተነሳ ሃሳብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ አቅጣጫ ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ