(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 03 ቀን 2015 .ም፤ አዲስ አበባ፤

ለሕዝብ ተወካዮች በምክር ቤት የቀረበውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምክር ቤቱ አማካሪ ኮሚቴ አጀንዳውን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

ሠሞኑን በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ  የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 1 () መሠረት ሐምሌ 29 ቀን 2015 . የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 መደንገጉ ይታወሳል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ግዜ አጀንዳ በተመለከተ የጉዳዩን አሳሳቢነት በጥልቀት አይቶና በሰፊው ተወያይቶ ለምክር ቤቱ ቀጣይ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲቀርብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአጀንዳነት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ታውቋል ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- 
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament 
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR 
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews 
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr 
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ