የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በአገልግሎት አሰጣጥ መምሪያ ሰነድ ላይ ተወያዩ 

(ዜና ፓርላማ)፣ ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በአገልግሎት አሰጣጥ መምሪያ ሰነድ በቢሸፍቱ እየተወያዩ ነወ።

ረቂቅ ሰነዱ ለውይይት የቀረበው ጽ/ቤቱ ባደራጃቸው አዘጋጅ ኮሚቴዎች ሲሆን የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ታምር ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸው ሰነዱ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ለማሳደግ የሚረዳ እና ካለንበት የለውጥ ወቅት ጋር የሚጣጣም ሆኖ መዘጋጀት ስላለበት ጥልቅ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።

በዚህም መሰረት ሰነዱ የቀረበበት መንገድና የተካተቱት ነጥቦች ትክክል መሆናቸውን ያነሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰነዱ ለተገልጋዮች ግልጽ ሆኖ መዘጋጀት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ሰነዱ የአገልግሎት ሰጭውንና ተቀባዩን ግንኙነት የሚያጠናክር እንዲሁም አገልግሎቱን በተቀመጠው የጥራትና የጊዜ ደረጃ ለመስጠት የሚረዳ በመሆኑ መነሻችን ተገልጋዩ ሊሆን ይገባል የሚሉና ሌሎች ሰነዱን ሊያዳብሩ የሚችሉ ሀሳቦች በመንሸራሸር ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ሰነድ ላይ ያለው ውይይት ሲጠቃለል በፓርላማ መረጃ መጽሐፍ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን የሁለቱንም ማጠቃለያ በነገው ዜና ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።