(ዜና ፓርላማ)፤ ሐምሌ 07፣ 2014 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የምክር ቤት አባላት ወደተመረጡበት አካባቢ ሲሄዱ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ ገለጻ ተደረገላቸው።

በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ አባላቱ በየደረጃው የተጀመሩ ስራዎችን ማገዝ እንደሚገባቸው ጠቁመው፤ ሰላምና ጸጥታ፣ የኑሮ ውድነት፣ መልካም አስተዳደር እና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በውክልና ስራው ትኩረት ሊሰጥባቸው እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማ እና የገጠር ግብርና፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የአካባቢ ጽዳት እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ላይ ህዝቡን በንቃት ማሳተፍ እንደሚገባ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ ወይዘሮ መሰረት ሀይሌ በበኩላቸው በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም አባላቱ ወደተመረጡበት አካባቢ ወርደው ማህበረሰቡን ባወያዩበት ወቅት የነበሩትን ጠንካራና ደካማ አሰራሮች አስታውሰው፤ አሁን በሚኖረው የውክልና ስራ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሰራሮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በ አበባው ዮሴፍ