(ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 19፣ 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የዜጎችን ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡

የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ የሚቀሩ ስራዎች ቢኖሩም ባለፉት 3 ዓመታት ካሪኩለም ከመቅረፅ ጀምሮ የመዋእለ ሕጻናት፣ የ1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን፣ የተማሪ ምገባ ማዕከሎችን የማስፋፋት እንዲሁም የፈተና ስርዓቱን የማሻሻል ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

ከጤና አኳያም በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ገና የሚቀር እና ብዙ ስራን የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

የዜጎችን መፈናቀል በተመለከተ የመልሶ ግንባታ ሰራዎች እየተሰሩና በቀጣይም ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመሆን እንደሚሰራ ጠቁመው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመግታት ግን ግጭቶችን ከምንጫቸው ማድረቅ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የዜጎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትን በተመለከተም ህጋዊ እስከሆኑ ድረስ መብታቸው ሊከበር እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

የማህበረሰቡን ሰላም የሚነሱና የተዛቡ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችን ሕዝቡ ባለመስማት እና መርጦ በመስማትና ከሚወስድባቸው እርምጃ ጎን ለጎን የህብረተሰቡን ሰላም ለማስከበር ሲባል በብሮድካስት ባለስልጣን በኩል ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድም ነው የጠቆሙት፡፡

ልማትን ለማፋጠንና የዜጎችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሙስናን መታገልም እንደሚገባም ነው ያብራሩት፡፡

በ ኃይለሚካኤል አረጋኸኝ

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ