የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የገቢዎች ሚኒስቴር ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የአሠራር ሥርዓቱን እንዲያዘምን ተጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህንን የጠየቀው ዛሬ በአካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብስባው የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የጉምሩክ ኮሚሽንን የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ህገወጥ የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር ለአገሪቱ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሊበለጽጉ እንደሚገባ እና የአሰራር ስርዓታቸውም መሻሻል እንዳለበት ምክር ቤቱ አስረድቷል፡፡

የፕላን፤በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 በጀት ዓመት እቅዱን ለማሳካት በአደረገው ጥረት የ10 ወራት አፈጻጸሙ 93 በመቶ መድረሱ የተሻለ ስራ እንዳከናወነ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል፤ ኮንትሮብንድን እና ህገወጥ የታክስ ማጭበርበር እና የታክስ ስወራን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፤ ችግሩ የሀገሪቱን ዜጎች ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሊያናጋ የሚችል በሽታ በመሆኑ ችግሩ አሳሰቢነት አንጻር የተቋሙ የአስራር ስርዓት ዲጂታላይዝድ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ባደረጋቸው ግምገማዎች የተቋሙ እቅድ ከክልል ቅርኝጫፍ መስሪያ ቤቶች ጋር ያለው የመረጃ እና የሪፖርት ልውውጥ የተናበበ መሆኑን፤ የገቢ አሰባሰቡ የተሸለ መሆኑን እንዲሁም ለታክስ ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን እና ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ማድረጉ በጥሩ ጎን የሚታይ እንደሆነ የተከበሩ አቶ ዳለኝ ገልጸዋል።

የታክስ ስርዓቱን ለማዘመን እና ኮንትሮ ባንድ ንግዱን ለመቀነስ ዲጂታላይዜሽን የማድረግ ስራው ጅምሩ ቢኖርም የበለጠ መስፋት እና መጠናከር እንዳለበት የተከበሩ አቶ ደሳለኝ አሳስበዋል፡፡

የቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያለው በበኩላቸው የኮንትሮባንድ ንግድ የፍትህ ሥርዓቱን የሚያዛባ እና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት ተግዳሮት በመሆኑ ማህበራዊ ተፅዕኖው የጎላ እንደሆነ ገለጸው፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ሁለንተናዊ ርብርብ በ2014 በጀት ዓመት ከ39 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የገር እና የህዝብ ሀብት ማዳን እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ከ282.5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንም እንደስኬት የሚገለጽ ቢሆንም ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በቂ ነው ሊባል እንደማይችልም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለጸጉ አሰራሮችን ስለሚከተሉ እነሱን የሚገዳደር ተቋም ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው፤ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ዘመና ተቋሙ በሰው ሀይል አደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዘርፉ የኮንትሮባንድ ንግዱንም ሆነ የታክስ ሰነድ ማጭበርበር እና ተያያዥ ችግሮችን ለለመቅረፍ በአንድ ተቋም በቻ የማይፈታ ችግር እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የችግሩን ስፋት እና አሳሰቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ ሊያርጉ እንደሚገባ ነው ያስረዱት፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ በበኩላቸው የህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ጸረ-ኮንትሮባንድ ግብረ-ሀይል በአዲስ አደረጃጀት ተዋቅሮ ወደ ስራ የገባ እንደሆነ ገልጸው፤ ችግሩን ለመከላክል በዚህ በጀት ዓት የተሰራው ስራ የሻለ ውጠየት የተገኘ ቢሆንም አሁንም የበለጠ በቅንጀት መስራት እንደሚያስፈልገ ነው ለምክር ቤቱ ያብራሩት፡፡

በ ተስፋሁን ዋልተንጉስ