"የሴቶች ተሳታፊነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚና እያደገ ነው” የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ
"የሴቶች ተሳታፊነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚና እያደገ ነው" የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ
(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 4 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እና የሴቶች ኮከስ የበላይ ጠባቂ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የሴቶች ተሳትፎና የውሳኔ ሰጭነት ሚና ከግዜ ወደ ግዜ እያደገ መምጣቱን ገለፁ፡፡
የምክር ቤቱ የሴቶች ኮከስ የ2017 በጀት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የቀጣይ ዓመት መሪ ዕቅድንና ለኮከስ አባላት በተለያዩ ረዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ሥልጠና አስመልክቶ ለኮኮስ ሥራአስፈፃሚና አባላት በተሳተፉበት መድረክ ላይ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እንደገለፁት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ምክር ቤት የሴቶች ውሳኔ ሰጭነትና ተሳትፎ እያደገ የመጣ መሆኑን ጠቁመው፤ ሴቶችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ኮከሱ ሚናውን በይበልጥ መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የምክር ቤቱ የሴቶች ኮከስ ተልዕኮውን ከመወጣት አንፃር በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አስታውሰዋል፡፡
በቀጣይም የተመራጭ ሴቶች ኮከስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ልምድ እና ተሞክሮዎችን በማስፋት ሀገራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አሳስበዋል፡፡
አሠራሮችን በማዘመንና ቴክሎጂን በመጠቀም የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል የኮከስ አባላት ተቀዳሚ ተልዕኮ ሊሆን እንደሚገባ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አያይዘው አስገንዝበዋል፡፡
ከዕቅድ ውይይቱ በተጨማሪ የጥናትና ምርምር ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives