Participate

የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ለማቋቋሚያና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ

የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ
ፈንድን ለማቋቋምና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ
የተጎሳቆለ መሬት መልሶ እንዲያገግም በማድረግ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለአገራችን ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና የሥነ ምህዳር ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግ በማስፈለጉ፣
ለአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ቋሚና ተቋማዊ ሥርዓት ያለው የፋይናንስ አቅም እንዲኖር ማስቻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በዘላቂነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም እና ከአየር ንብረት ብክለት የፀዳ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተያዘውን አገራዊ ራዕይ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ማድረግ በማስፈለጉ፤
እነዚህን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተቀናጀ ቋሚና ዘላቂነት ያለው የሀገር ውስጥ የፋይናንስ ምንጭ በመመደብና በማሰባሰብ ሁሉም ክልሎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር መቀየስ ተገቢና ለዚኅም የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

Vote