የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ - Draft Laws
Participate
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ
Portal Admin, modified 4 Months ago.
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ
Youngling Posts: 16 Join Date: 1/22/18 Recent Posts
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀፅ 40(7) የተደነገገውን ዜጎች በመሬት ላይ ለሚያፈሩት ቋሚ ንብረት የተጎናጸፉት የባለቤት እና በመሬት የመጠቀም መብታቸውን በከተሞች ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ከመጀመሩ አስቀድሞ መከናወን የሚገባቸው የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እንዲሁም የማረጋገጥ፣ የምዝገባና የአገልግለት አሰጣጥ ተግባራት በግልፅ መቀመጥ ለካዳስተር አተገባበር ወሳኝ በመሆኑ፤ ስራዎቹን ለመተግበር በህግ ኃላፊነት ለተሰጣቸው አካላት የተጠያቂነት ስርዓት ማስፈን በማስፈለጉ፤
የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ስራን ሊያቀላጥፍ፣ ሊያሳጥርና ውጤታማ ሊያደርግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ዜጎች ላይ ሊከሰት የሚችልን እንግልት በማስቀረት፣ ፈጣንና የዘመነ አገልግሎት መስጠት በማስፈለጉ፤
የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባን በዘመናዊ መረጃ አያያዝ ስርዓት ገንብቶ በመዘርጋት በአገር-አቀፍ ደረጃ ወጥነት ባለው መልኩ በማደራጀትና በመተግበር በሁሉም ከተሞች ውስጥ የሚገኙትን የመሬት ይዞታ መረጃ ማደራጀት በማስፈለጉ፤
በእያንዳንዱ የመሬት ይዞታ ላይ የሚገኝን መሬት ነክ ንብረት ከቁራሽ መሬት ይዞታው ጋር አስተሳስሮ ለመመዝገብ፣ መረጃውን ለማደራጀትና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል መነሻ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፣