Participate

የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ

Portal Admin, modified 1 Month ago.

የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ

Youngling Posts: 15 Join Date: 1/22/18 Recent Posts
ባንኮች ገንዘብ በማሰባሰብ እና ወደተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በማሰራጨት ለኢኮኖሚ ልማት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የክፍያና የሂሳብ ማወራረድ ሥርዓት ውስጥ ቁልፍ ቦታ የሚይዙ በመሆኑ፤
ጥንቃቄ በተዘጋጀ የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፍ መሰረት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ የዘርፉን ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት በማሻሻል ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ የሚታመን በመሆኑ፤
አዋጭነቱ ያበቃ እና መልሶ አዋጭ የመሆን ተስፋ የሌለው ተደርጎ የሚቆጠር ማንኛውም ባንክ ከፍተኛ የሥርዓት መናጋትን እና ኪሳራን በማያስከትል መልኩ እልባት ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑ በርካታ የተለያዩ ሥልጣኖችን እና አማራጮችን ለእልባት ሰጪ ባለሥልጣን አካሉ ማለትም ለብሔራዊ ባንክ የሚሰጥ ውጤታማ የእልባት ሥርዓት መኖር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የባንክ ሥራ በአግባቡ ካልተመራ በፋይናንስ ሥርዓቱና በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ያለመረጋጋትን ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ፤
የፋይናንስ ሥርዓትና የማክሮ ኢኮኖሚ ያለመረጋጋት ሕዝብን እና መንግሥትን ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ፤
የባንክ ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥንና ቁጥጥርን በሚመለከት በአሁኑ ወቅት ካለው እና ለወደፊቱ ከሚኖረው የዘርፉ ለውጥ ጋር የሚጣጣም ሁሉን አቀፍ የሕግ ማዕቀፍ በመዘርጋት የባንክ ሥራን ደህንነት፣ ጤናማነትና መረጋጋት ቀጣይነት ባለው መልኩ ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
​​​​​​​

Vote