የፌደራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ - Draft Laws
Participate
የፌደራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ
Portal Admin, modified 3 Months ago.
የፌደራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ
Youngling Posts: 16 Join Date: 1/22/18 Recent Posts
የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸው ስልጠናዎች እና ሌሎች የሚያከናውናቸው ተግባራት ለዳኝነት እና የፍትህ አካላት ቢሆንም ተጠሪነቱ አስፈፃሚ አካሉ ጋር መሆኑ የዳኝነት አካሉን ፍላጎት በአግባቡ አሟልቶ ሥራውን ከመምራት እንፃር ክፍተት የሚታይ ከመሆኑም በተጨማሪ የዳኝነቱን አካሉን ነፃነትና እና ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚስገባ ሆኖ በመገኘቱ፤ ተጠሪነቱ ለዳኝነት አካሉ የሆነ፣ ስራውን በአግባቡ ለማከናወን የሚስችል የሰው ሀይል እና የአሰራር አደረጃጀት ያለው የፍትህና ሕግ ተቋም በማቋቋም በእውቀቱ፣ በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ፣ እንዲሁም በሥነ-ምግባሩ ብቁ የሆነና የተሟላ ስብዕና ያለው የዳኝነት እና የፍትህ አካላት አመራር እና ባለሙያ ማፍራት ለፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ሕጎችን ከወቅታዊ የአገሪቱ የዕድገት ደረጃ ጋር የተጣጣሙ ለማድረግ እንዲሁም የዳኝነት፣ የፍትህ አካላትና ሌሎች ከፍትህና ሕግ ሥራ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላትን ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ ጥናትና ምርምሮችን ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአገሪቱ የፍትህ ዘርፍ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እያሳካ ስለመሆን አለመሆኑ የሚያሳይ አስተማማኝና የተሟላ የፍትህና ሕግ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማደራጀት የሚችል በቂ የሰው ሀይል እና አግባብነት ያለው የአሰራር እና አአደረጃጀት ሥርዓት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በፍትህ ሥርዓቱና በሕግ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረጉ የማሻሻያ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመምራትና ለማስፈጸም የሚያስችል አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤