null የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ

Tigist T, modified 11 Months ago.

የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ

Youngling Posts: 23 Join Date: 3/15/18
የአገራችንን ሁለንተናዊ እድገትና የፈጠራና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማረጋገጥ፣ በእውቀትና በክህሎት የጎለበተ የሰው
ኃይልና ማህበረሰብ ለማፍራት የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ
ትስስር ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፤
የከፍተኛ ትምህርት፣ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እና የምርምር ተቋማት ከኢንዱስትሪ ጋር ያላቸው የትስስር ሥራዎች
እንዲሁም የዋና ዋና ተዋናዮችን ግዴታንና ኃላፊነትን በግልጽ በህግ መደንገግ ትስስሩን በአገር አቀፍ ደረጃ
በእያንዳንዱ ተቋም ውስጥ በውጤታማነት፣ በተጠያቂነት፣ በተዓማኒነት እና ወጥ በሆነ መልኩ በቅንጅት
እንዲከናወኑ የሚያደርግ ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ በምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪ መካከል አጋርነትንና ትብብርን
ለማሳደግ፤የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች እና የምርምር አጀንዳዎች በመቅረጽ የተቋማቱን አቅም የሚገነባና
የኢንዱስትሪውን ችግር የሚፈታ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ የተመላከቱ የትስስር ጉዳዮችን ወደ ህግ ድንጋጌ በማሳደግ
የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የፈጠራ ሥራዎችን በሚፈለገው ደረጃ ለመተግበር የሚያስችል በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሰረት የከፍተኛ ትምህርትና
ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ ወጥቷል፡፡