null የግብርና ምርት አምራችና አስመራች ግንኙነትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ

Tigist T, modified 1 Year ago.

የግብርና ምርት አምራችና አስመራች ግንኙነትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ

Youngling Posts: 23 Join Date: 3/15/18
የግብርና ምርትን ጥራት፣ የአመራረት ቅልጥፍናንና ተወዳዳሪነት እንዲሁም የግብርና እና አግሮ- ኢንዱስትሪ ተመጋጋቢነት በማሳደግ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እውን ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑ፤
የግብርና ምርት አምራቾች ለገበያ የሚሆን የግብርና ምርቶችን ወደ ማምረት በማሸጋገር የግብርና ምርቶችን ከሚያዘጋጁ፣ ከሚያቀነባብሩ፣ እሴት ከሚጨምሩ አግሮ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ከትላልቅ ገዥዎች ጋር ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር መፍጠር ወሳኝ በመሆኑ፤
በሥራ ላይ ያሉት ሕጎች የግብርና ምርት ውልን ልዩ ባሕሪያት በተሟላ መልኩ የማያስተናግዱ በመሆናቸው፤ የግብርና ምርት ውልን በመጠቀም ማምረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የእውቀትና ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት የአምራች እና የአስመራች ግንኙነት በተሟላ የሕግ ማዕቀፍ የሚመራበት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግስት አንቀጽ 55(6) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡