ምክር ቤቱ ለኮሚሽኑ የተሰጠው ኃላፊነት ከፍተኛ በመሆኑ ከህዝብ የተሰጠውን አስተያየት መነሻ በማድረግ  ብዝኃነትን ለማረጋገጥ በተለይም ፆታና ዕድሜ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አንድ አንድ እጩዎች በሰጡን ሃሳብ መነሻነት ተጨማሪ እጩዎችን በማካተት ለአስተያየት ከቀረበ ቦኃላ 11 የምክክር ኮሚሺን አባላትን መርጧል፡፡   

በወቅቱ እጩ ሆኖ የቀረቡ ኮሚሺነሮች

Ato Abate Kisho Hora
Education Level: ማስተርስ ዲግሪ
Experience

ለ10 አመታት ደቡብ ኢትዮጵያን በርእሰ መሰተዳደርነት የመሩ፣

Dr. Abdisa Zeray Bemano
Education Level: ሁለት ማስተርስ ዱግሪ
Experience

በጆርናሉዝም እና ኮሚዉኒኬሽን ት/ት ክፍል ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል፤ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ባለስልጣን ቦርድ አባል የነበሩ፤ በመንግስት እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሀከል ተከታታይ የዉይይት ባህል እንዲዳብር የሰሩ፤ በመካከለኛዉ አፍሪካ ሀገራት እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርምር ያካሄዱ

Dr. Abera Deresa
Education Level: PHD
Experience

በርካታ የምርምር ስራዎችን ሰርተዋል፤ የተለያዩ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመጎብኘት ለሀገረችን የሚመጥን ልምድ እንዲቀመር አድርገዋል። በሰላም፤ በልማትና በማህበራዊ አገልግሎት ከፍተኛ ድጋፍ ያበረከቱ

Prof. Afework Bekele Simegn
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

ከፍተኛ ተመራማሪ፤ ከ335 በላይ የምርምር ወረቀቶችን ያሳተሙ፤ የሳይንስ ፋክሊቲ ዲን የነበሩ፤ የተለያየ የሙያ ማህበራት ጋር በመሳተፍ አስተዋፅኦ ያበረከቱ

Ato Ahmed Hussen Mohammed
Education Level: በህግ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ
Experience

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ም/ቤት ም/ፕሬዘዳንት፤ በሰብሳቢ ዳኝነት፤ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን የቦርድ አባል

Dr. Ambaye Ogato Anata
Education Level: በሶሻል አንትሮፖሎጂ ፒኤችዲ
Experience

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት፤ እና በአሁኑ ሰዓት በሰላምና ዲያሎግ ከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ያሉ፤ በማክስ ፕላንክ የስነ ህዝብ ጥናት ተቋም ያገለገሉ እና በዚሁ ተቋም የማህበራዊ አንትሮፖሎጂ ተቋም በግጭትና ውህደት ክፍል ውስጥ የድህረ ዶክትሬት ጥናት አድርገዋል

Ato Andargachew Asegid
Education Level: የመጀመሪያ ዲግሪ
Experience

ፀሀፊ፤ ለህዝብ ነፃነት የታገሉ፤ ለሰላምና ለእርቅ የሰሩ፤ በተለያዩ ሰብዓዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ፤

Dr. Ayrorit Mohammed Yasin
Education Level: ፒኤችዲ በህግ
Experience

አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ፤ በተለያየ የሀላፊነት ቦታ የሰሩ::

Prof. Baye Yimam
Education Level: ፒኤችዲ በማህበረሰብ ቋንቋ ጥናት
Experience

በአአዩ መምህርና ተመራማሪ፣ ከ30 በላይ ጥናቶችን ያሳተሙ፤ በቋንቋ ፖሊሲ ዝግጅት ወቅት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ

Dr. Bedilu Wakjira
Education Level: PHD
Experience

በሰሯቸው ጥናታዊ ስራዎች፣ ድርሰቶችና ማህበረ-ፖለቲካዊ ሂሶች የሀገራችንን ችግር ነቅሰው በማውጣት የመፍትሄ ሀሳቦችን ከመጠቆም ባለፈ ያለምንም ፍርሃት ላመኑብት እውነት የቆሙ

Prof. Bekele Gutema Jebesa
Education Level: ፒኤችዲ በፊሎሶፊ
Experience

ከፍተኛ የማህበረዊ ሳይንስና የፍለስፍና እውቀት ያላቸው፣ ትሁትና ታታሪ

W/ro Bilen Gebremedhin Yosef
Education Level: Master Degree
Experience

የህግ መምህር የነበሩ፤ የአለም አቀፍ ልማት ማዕከል ቢሮ ሀላፊ የነበሩ፤ በቀይ መስቀል ማህበር ውስጥ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው የሰሩ፤ በሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያገለገሉ ያሉ::

Prof. Daniel Kitaw
Education Level: ፒኤችዲ በቴክኖሎጂ
Experience

በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዲን፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መስራች አባል፤ የኢትዮጵያ ስካር ኮርፖሬሽን አባል፤ የተለያዩ ተቐማት የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል

Dr. Dawit Yohanes
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በአፍሪካ ቀንድ ያሉ የምክክር ኮሚሽን ልምዶችን የቀመረና የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ያቀረበ፤ በሰላምና ደህንነት ተቋም በርካታ የምርምር ጥናቶችን ያከናወኑ

Ato Gemechu Dubiso Gudena
Education Level: ማስተርስ ዲግሪ
Experience

ዋና ኦዲተር ሆነው ሀገራቸውን ለረዥም ጊዜ ሀላፊነታቸውን በታማኝነት የተወጡና ያገለገሉ

Prof. Habtamu Wondimu
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ 40 ዓመታት በላይ ያገለገሉ፤ በትምህርት ክፍል ሃላፊነት፣ በትምህርትና ባህርይ ጥናት ኮሌጅ ዲንነት፣ በመምሪያ አስተባባሪነት፣ በሙያ ማህበራት መሪነት፣ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀትና በመምራት ወዘተ በብቃት አገልግለዋል፡፡ ያደረጓቸው ከ100 በላይ የምርምር ሥራዎቻቸው በአገር ጉዳዮች በተለይም በትምህርት፣ በብዝሃነት፣ በሰላምና ግጭት ጉዳዮች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ፤ በርካታ ሽልማቶችንና ዕውቅናዎችን ከአገርና ከአገር ውጭ ያገኙ፤

Ato Haile Gebre Suse
Education Level: ማስተርስ ዲግሪ
Experience

ዘመናዊ የህብረት ስራ ማህበር እንዲቋቋም ብርቱ ጥረት ያደረጉ፤ በፌዴራልና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ኤጄንሲ በርካታ ኃላፊነቶችን በብቃት የተወጡ፤ በኦሮሚያ ተከስቶ ለነበረው የጸጥታ ችግር መፍትሄ በማፈላለግ ግንባር ቀደም የነበሩ እና ከፍተኛ ህዝባዊ ተቀባይነት ያላቸው

W/ro Hirut G/Silassei Oda
Education Level: ህግ ማስተርስ
Experience

የተመድ ልዩ መልእክተኛ ሆነው ያገለገሉ፤ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ::

Prof. Hizkias Assefa
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በሰላምና እርቅ ዙርያ ከ50 በላይ አገራት በመዘዋወር ሰርተዋል፡፡ ለተ/መ/ድ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ለተለያዩ አለምአቀፍና አገር በቀል መ/ያ/ዶች በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም በግጭት አፈታት፣ በሰላምና እርቅ ዙርያ በርካታ ሴሚናሮችና አውደ-ጥናቶች ከማካሄዳቸውም በላይ ብዙ መጽሐፍትንና መጣጥፎች አበርክተዋል። ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሪላንካ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮሎምቢያ፣ ጓቲማላ ወዘተ የሰላምና እርቅ ውይይቶችን በመምራት የተሳካ ስራ ሰርተዋል::

Ato Ibrahim Mulushewa Ishete
Education Level: በታሪክ የመጀመርያ ዲግሪ የማስተርስ ዲግሪ
Experience

የብሔራዊ እና ክልላዊ የውህደት ጥናት ማዕከል (CeNRIS) መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፣የጥናት ማእከሉ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች መካከል ያለውን መግባባትና ውህደት ደረጃውን በማሳደግ ረገድ ይሰራል. አቶ ኢብራሂም በአገርአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የልማት፡ የሰላም፤ የሰብአዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በንቃት ይሳተፋሉ፤ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ተቋማት ጋር ይሰራሉ፡፡

Prof. Kasahun Birhanu Alemu
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ምክክሮች በአባልነትና በአመራርነት የሰሩ፤ ትውልድን ከመቅረፅ አንፃር በዙ ጥናቶችንና ምክረ ሀሳቦችን ያበረከቱ

Prof. Kifle W/Mikael Hajeto
Education Level: ፕሮፌሰር
Experience

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በቦርድ አባልነት ያገለገሉ፤ በዙ የምርምር ጥናቶች ያቀረቡ፤ በተለያየ የምርምር ተቐማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያገለገሉ፤

Ato Melaku W/Mariam Baliye
Education Level: በህግ የመጀመርያ ድግሪ
Experience

ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ በህዝባዊ ተቋማት በርካታ ሁኔታ አገልግሎት የሰጡ; በሽግግር መንግሰት ምክር ቤት በህግ አማካሪነት፤ በመንግስት ምክር ቤት በህግ ባለሙያነት፤ በኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ዋና ፀሀፊነት፤በልማት ማህበራት በአመራርነት

Prof. Mesfin Araya Weldetensay
Education Level: ፒኤችዲ በአእምሮ ህክምና
Experience

በአእምሮ ህክምና ዘርፍ ከ30 አመታት በላይ ያገለገሉ፣ ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያሳተሙ፣ብሄራዊ ኤችአይቪ ስክሬታሪያት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፣ በተለያዩ የሀገራችን ከፍሎች በመዘዋወር ሆስፒታሎችን መርተዋል፡፡ በአአዩ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በኃላፊነት ያገለገሉ፤ በተለያዩ ሀገራዊ የሰላም መድረኮች በሚያቀርቧቸው አስተማሪና መካሪ ሀሳቦች በመነሳት ለሀገራዊ መግባባት እየሰሩ ያሉ::

Dr. Minas Hiruy
Education Level: PHD
Experience

የህዳሴ ግድብ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት አባል፤ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በቦርድ አባልነት ያገለገሉ፤ ብዙ የሰብአዊ እርዳታ በማድረግ የሚታወቁ፤ በደቡብና አማራ ክልል ላደረጉት አስተዋጽኦ የተሸለሙ

Ambassador Mohamed Dirir Gehadi
Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ
Experience

በምክር ቤት አባልነት፤ በአምባሳደርነት፤ በሚንስቴርነት፤ በከፍተኛ አማካሪነት፤ በኢጋድ አስተባባሪነት፤ በሱዳን ልዩ መልእክተኝነትና በአፍሪካ ቀንድ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው።

Ambassador Muez G/hiwot W/silassie
Education Level: ድግሪ/በማኔጅመንት
Experience

በሰብአዊ ጉዳይ ስራዎች፣ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች፣ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በመቻቻል፣ በመከባበርና በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የእርቅና የሽምግልና ተግባራት በመከወንና፤ ነፃ የሕብረተሰብ አገልጋሎት በመስጠትና፤ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የፍትህ ጥያቄዎች በማጋለጥ ይታወቃሉ

Ato Mulugeta Ago W/Michael
Education Level: Masters
Experience

በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንትነት፤ ም/ፕሬዘዳንትነትና ዳኝነት ያገለገሉ በከፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንትነትና ዳኝነት ያገለገሉ

Dr. Negalign Birhanu Baye
Education Level: ፒኤችዲ በአለም አቀፍ ጤና
Experience

የረዥም ጊዜ የማስተማር ልምድ ያላቸው፤ የማህበረሰብ ዓቀፍ አገልግሎት፤ በርካታ የምርምር ስራዎችና ህትመት ያላቸው፡፡

Ato Nigusu Aklilu
Education Level: ማስተርስ ዲግሪ
Experience

ፎረም ፎር ኢንቫይሮንመነት የሚባል ሀገር በቀል ተቋም ያቋቋሙና ዘላቂ ልማት ለሀገራችን ሰላም፣ እድገት ያለውን ፋይዳ ያሳወቁ፣ የማወያየት አቅም ያጎለበቱ፣ ዴስቲኒ ኢትዮጵያን ያቋቋሙ፣

Ato Samuel Tassew Tefera
Education Level: በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ
Experience

በ 34 የመንግስት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአማካሪነት ያገለገሉ፤ በተለያዩ ሀገራት በህግ ዙሪያ ስልጠና የሰጡ፤

Dr. Semir Yesuf
Education Level: በፖለቲካ ሳይንስ ፫ኛ ዲግሪ
Experience

በምክክር ስራዎች ዙሪያ አለምአቀፍ ተሞክሮዎችን ጨምሮ ጥናት ያደረጉ፤ በሰላምና ጸጥታ በግጭት አፈታትና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ጥናቶችን ያቀረቡ

Ambassador Tadelech H/Mikael
Education Level: Master Degree
Experience

የመጀመርያ የሴቶች ሚንሰትር በኮትዲቯር እና ፈረንሳይ አምባሳደር፣አፍሪካ ህብረት በተለያዩ ሀገራት ምርጫ ታዛቢነት፣

Dr. Takele Seboka
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

ተመራማሪ፤ የፖሊሲ አማካሪ ሆነው ያገለገሉ፤ ዳኛ ሆነው ያገለገሉ፤ ብዙ ምርምር ጥናቶችን ያሳተሙ

Dr. Tegegnework Getu Mengesha
Education Level: ፒኤችዲ እና ሁለት ማስተርስ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካ
Experience

በተመድ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ፤በ ሀገራት የልማት ፕሮግራሞች የመሩ፤ በርካታ ፅሁፎችን ያበረከቱ፤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያስተማሩ፤ የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ፤ ግጭቶችን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው፤የተመሰከረ የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ያላቸው::

W/rt Teklehaimanot G/Ayezigi
Education Level: Master
Experience

መምህር ሆነው እያገለገሉ ያሉ፤ ጋዜጠኛ ሆነው ያገለገሉ፤ በህዝብ ዘንድ ጥሩ ተቀባይነት ያላቸው

Ato Tesfaye Habiso
Education Level: ማስተርስ ዲግሪ
Experience

በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት በከፍተኛ ስራ ሃላፊነት፣ በደቡብ አፍሪካ እና በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የሽግግር መንግስት ዋና ጸሀፊ

Prof. Tilahun Teshome
Education Level: የህግ ፕሮፌሰር
Experience

የረዥም ጊዜ የፍርድ ቤትና የማስተማር ልምድ ያላቸው፣ በአአዩ መምህርና ተመራማሪ፣ የ2013 በማህበራዊ ዘርፍ የበጎ ሰው ተሸላሚ

W/rt Tinebeb Birhane G/Meskel
Education Level: Master
Experience

በተለያዩ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በሀላፊነት ያገለገሉ፤ ፤ለሴቶች ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፅኦ ያደረጉ፤

Loret Prof. Tirusew Tefera
Education Level: PHD
Experience

በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤት ያላቸው፤ በሀገራችን በትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያው ባለሙሉ ፕሮፌሰር፤ ከተባበሩት መንግስታትና ሌሎች ተቋማት ዕውቅና ያገኙ

Dr. Wedajo W/Giorgis
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

በዩኒቨርስቲ መምህርነት ያገለገሉ

Prof. Yaekob Arsano
Education Level: ፒ ኤች ዲ በፖለቲካል ሳይንስ፣ ማስተርስ አፍሪካን ስተዲስ ኤንድ ኮምፓራቲቭ ፖሊቲክስ፣ ቢኤ ፖሊቲካል ሳይንስ ኤንድ ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ
Experience

በደቡብ አፍሪካ የኦኤዩ የምርጫ ታዛቢ (1994 እ.ኤ.አ)፣ Chairman advisory council for north – south research for sustainable mitigation of development and conflict problems in the horn of Africa(2006 – 2016), national leader for water and society project in Northeastern Africa( 2014 – 2019), National leader for water essence Africa project(on going: 2021 – 2026), ድንበር ዘለል ውሃዎች ድርድር የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ፣ የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ National Panel of Experts (NPoE) ምክትል ሰብሳቢ፣ የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ብሄራዊ ምር ቤት አባል፣የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የ international Panel of Experts (IPoE) አማካሪ፣የወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባል፣

Dr. Yonas Adaye Adeto
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

ተመራማሪ፤ አሰልጣኝ::

Ato Zegeye Asfaw Abdi
Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ
Experience

ላለፉት 40 አመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ አገልግሎት የሰጡ::

Prof. Zekarias Kenea Tesgera
Education Level: በህግ ሁለተኛ ድግሪ
Experience

በአአዩ የህግ መምህር እና ተመራማሪ፤ በርካታ የምርምር ስራዎችን ለህትመት ያበቁ፣ በህግ ማሻሻያ ካውንስል በጎ ፍቃድ አባል በመሆን ለህግ መሻሻያዎች ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ፣ ሀገር ወዳድና የሀገር ሽማግሌ

W/ro Zenebework Tadese Markos
Education Level: ማስተርስ በስነ ህዝብና በህግ
Experience

በሀገር ውስጥ፥ በብዙ የአፍሪካ ሀገራትና ዓለም አቀፍ መድረኮች ሰፊ ጥናቶች፥ ፅሁፎች፥ የማማከር ሥራዎችን በማህበራዊ ልማት፥ በመልካም አስተዳደር፥ በሴቶች ተሳትፎና መብት ዙሪያ እያበረከቱ ያሉ፤ በተለያዩ የሞያ ማህበራት፥ ትምህርት ተቋማት፥ መንግስታዊ ባልሆኑ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በተለያዩ የአባልነት፥ ሀላፊነት ቦታዎች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የተሳተፉ

በወቅቱ እጩ ሆኖ ከረቡት ውስጥ በምክር ቤቱ የተሾሙ ኮሚሺነሮች

Prof. Mesfin Araya Weldetensay
Education Level: ፒኤችዲ በአእምሮ ህክምና
Experience

በአእምሮ ህክምና ዘርፍ ከ30 አመታት በላይ ያገለገሉ፣ ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያሳተሙ፣ብሄራዊ ኤችአይቪ ስክሬታሪያት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፣ በተለያዩ የሀገራችን ከፍሎች በመዘዋወር ሆስፒታሎችን መርተዋል፡፡ በአአዩ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በኃላፊነት ያገለገሉ፤ በተለያዩ ሀገራዊ የሰላም መድረኮች በሚያቀርቧቸው አስተማሪና መካሪ ሀሳቦች በመነሳት ለሀገራዊ መግባባት እየሰሩ ያሉ::

W/ro Hirut G/Silassei Oda
Education Level: ህግ ማስተርስ
Experience

የተመድ ልዩ መልእክተኛ ሆነው ያገለገሉ፤ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ::

W/ro Bilen Gebremedhin Yosef
Education Level: Master Degree
Experience

የህግ መምህር የነበሩ፤ የአለም አቀፍ ልማት ማዕከል ቢሮ ሀላፊ የነበሩ፤ በቀይ መስቀል ማህበር ውስጥ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው የሰሩ፤ በሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያገለገሉ ያሉ::

Dr. Ayrorit Mohammed Yasin
Education Level: ፒኤችዲ በህግ
Experience

አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ፤ በተለያየ የሀላፊነት ቦታ የሰሩ::

Dr. Ambaye Ogato Anata
Education Level: በሶሻል አንትሮፖሎጂ ፒኤችዲ
Experience

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት፤ እና በአሁኑ ሰዓት በሰላምና ዲያሎግ ከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ያሉ፤ በማክስ ፕላንክ የስነ ህዝብ ጥናት ተቋም ያገለገሉ እና በዚሁ ተቋም የማህበራዊ አንትሮፖሎጂ ተቋም በግጭትና ውህደት ክፍል ውስጥ የድህረ ዶክትሬት ጥናት አድርገዋል

Ato Zegeye Asfaw Abdi
Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ
Experience

ላለፉት 40 አመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ አገልግሎት የሰጡ::

Dr. Yonas Adaye Adeto
Education Level: ፒኤችዲ
Experience

ተመራማሪ፤ አሰልጣኝ::

Dr. Tegegnework Getu Mengesha
Education Level: ፒኤችዲ እና ሁለት ማስተርስ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካ
Experience

በተመድ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ፤በ ሀገራት የልማት ፕሮግራሞች የመሩ፤ በርካታ ፅሁፎችን ያበረከቱ፤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያስተማሩ፤ የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ፤ ግጭቶችን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው፤የተመሰከረ የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ያላቸው::

Ato Mulugeta Ago W/Michael
Education Level: Masters
Experience

በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንትነት፤ ም/ፕሬዘዳንትነትና ዳኝነት ያገለገሉ በከፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንትነትና ዳኝነት ያገለገሉ

Ambassador Mohamed Dirir Gehadi
Education Level: በህግ የማስተርስ ድግሪ
Experience

በምክር ቤት አባልነት፤ በአምባሳደርነት፤ በሚንስቴርነት፤ በከፍተኛ አማካሪነት፤ በኢጋድ አስተባባሪነት፤ በሱዳን ልዩ መልእክተኝነትና በአፍሪካ ቀንድ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው።

Ato Melaku W/Mariam Baliye
Education Level: በህግ የመጀመርያ ድግሪ
Experience

ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ በህዝባዊ ተቋማት በርካታ ሁኔታ አገልግሎት የሰጡ; በሽግግር መንግሰት ምክር ቤት በህግ አማካሪነት፤ በመንግስት ምክር ቤት በህግ ባለሙያነት፤ በኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ዋና ፀሀፊነት፤በልማት ማህበራት በአመራርነት