የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
null የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
Zewidnesh L
Modified 3 Years ago.
የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባር እና ኃላፊነት
የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያከናውናል፡-
- የአገርና የሕዝብ ሰላም፣ ድህነትና ነፃነት እንዲከበሩ የሚያስችል ስልት የተነደፈ መሆኑና አስፈላጊው ግንዛቤና የንቅናቄ ስራ መከናወኑን፤
- በየትኛውም የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች መብትና ነፃነታቸው በተሟላ እንዲከበርና ጥበቃ እንዲያገኝ የፌደራሉ መንግስት ከክልል መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን፤
- በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ብሔራዊ መግባባት ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን፤
- መንግስት የሚፈራረማቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚያረጋግጡና ሉዓላዊነትን የሚያስከብሩ፣ ከውጭ ግንኙነት መርሆና ፖሊሲ ጋር የተጣጣሙ መሆኑን፤
- መንግስት የሚያካሂዳቸው የውጭ ግንኙነት ተግባራት የአገሪቱን ዘላቂ ሰላም፣ ዲሞክራሲና ልማት የሚያረጋግጡ መሆኑን፤
- የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም እቅዶችና ህጎች በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውንና የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘታቸውን፤
- የአገሪቷ የግዛት ሉዓላዊነት እየተከበረ መሆኑን፤
- የአገሪቱን ሉዓላዊነት ሊያስከብር የሚችል የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ተዋፆ የጠበቀ የመከላከያ ሰራዊት መደራጀቱን፤
- የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የስራ ሁኔታና አስተዳደር በአግባቡ መጠበቁን፤
- ከሌሎች አገራት ጋር የሚደረጉ ወታደራዊ ስምምነቶችና አፈፃፀሞች፤
- ክፍለ አህጉራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ የሰላም ስምምነቶችን፣ ግዴታዎችና አፈጻጸሞችን በተመለከተ፤
- የአገር መከላከያ ሰራዊት በሌሎች አገራት የሚያካሂዳቸውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች፤
- ለሕገ-መንግሥቱና ለሕገመንግሥታዊ ስርዓቱ በታማኝነትና በፅናት የሚቆም፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዘመናዊና ጠንካራ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት መገንባቱን፤
- ጥራት ያለው መረጃ በማቅረብና አስተማማኝ የደህንነት አገልግሎት በመስጠት የአገሪቷ ብሔራዊ ደህንነት እየተጠበቀ መሆኑን፤
- በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራትን፣
- የህዝብ ሠላም መጠበቁን እንደዚሁም አለመግባባቶችንና ግጭቶችን ለመከላከልና በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል አሠራርና እንቅስቃሴ መኖሩን፤
- በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል በመግባባትና በአጋርነት ላይ የተመሠረተ መልካም ግንኙነትና ትብብር እንዲጠናከር የሚደረገውን እንቅስቃሴ፤
- የአገሪቱን የመከላከያ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አፈፃፀምን፤
- የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸውን፤
- የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡና በውጤታማነት በስራ ላይ ማዋላቸውን፡፡