Participate

የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ

የሕዝብ በዓላት ለዜጎች ሥነ-ምግባርና ስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ለሀገርና ለህዝብ ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ እውቅና መስጠት እና በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሕዝብ በዓላት ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ሥርዓታቸውን ጠብቀው የሀገር እና የህዝብን ክብርና ጥቅም በሚያስጠብቅ ሁኔታ በሰላም፣ በድምቀት እና የዜጎችን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ በሚያጎለብት መልኩ እንዲከበሩ ለማድረግ የበዓላቱን አከባበር በሕግ መደንገግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

Vote