ይሳተፉ

የፌደራል መንግስት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ

Tigist T, modified 4 Months ago.

የፌደራል መንግስት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ

Padawan Posts: 29 Join Date: 15/03/18 Recent Posts
1. መግቢያ
የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች፡-
 የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ በግልጽ፣ በውድድርና ብቃት ወይም ሜሪት ላይ እንዲመሰረት እና ስራን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ፣
 የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደርን ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎት እና ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስርአት አስፈላጊ ሆኖ በመሆኑ፣
 የብሔር ብሔረሰቦች፣የአካል ጉዳተኞች፣ የፆታ ተዋጽኦ እና የመሳሰሉትን ብዙሀነት እና አካታችነትን ያገናዘበ ኢትዮጵያን የሚመስል የመንግስት ሠራተኞች ስብጥርን ከግምት ውስጥ ያስገባ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ፣
 የመንግስት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓትን መዘርጋት፣በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማስፈፀም፣ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማግኘት እና በሥራ ላይ ያሉትንም ለማቆየት፣
 የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ኀላፊነት፣ ተግባር እና ተልዕኮ በብቃት፣ በጥራት እና በውጤታማነት እንዲወጡ ለማድረግ፣
 ዘመናዊ የሆኑ የአሰራር ሥርዓትን፣ ሥልትን እና ዘዴን በመጠቀም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡
 በሰራተኞች መካከል ጤናማ ተወዳዳሪነት እንዲኖር፣ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የማትጊያ እና ማበረታቻ ስርአትን ለመመስረት፣
 የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስራ ለማሻሻል፣ ምርታማነት ለመጨመርና ለማጎልበት ረዥም ጌዜ የሚወስዱ ጉዳዮች በማስተካከል እና ለሥራ ሰፊ ጊዜ መስጠት በማስፈለጉ፣
 ​​​​​​​አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በስራ ላይ ከዋለ በኋላ በትግበራ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት፣ የመንግስትን መፈጸም ብቃት ማጎልበት፣ የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካና አለም ወደ የደረሰበት የእድገት ደረጃ ሊያሸጋግር የሚያስችል የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡
can we have the draft ?
You forgot to attach the draft proclamation
የክልል እና የፌደራል ሰራተኞች በሰፊ ልዩነት ነው እየተዳደርን ለነው። ለምሳሌ የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ቤት ወይም ቤት መስሪያ ቦታ እያገኙ ነው የፌረዳል ሰራተኞች ግን ስንጠይቅ የፌደራል ቦታ የለውም እየተባለ ነው። አዲስ አበባ ላይ መኖር አልቻልንም። ፈጣን መፍትሔ ያሻዋል። ጉዳዩ በመነሳቱ በጣም ደስ ብሎናል በርቱልን!!

ይምረጡ