ይሳተፉ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገለግሎት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት ከተቀመጡት መሰረታዊ መብቶች አንዱ የሆነውን የመዘዋወር ነፃነቶች ማስከበር ያስችለው ዘንድ ለኢትዮጵያውያንና ለውጭ አገር ሰዎች ሕጋዊ የጉዞ ሰነድና ቪዛ በመስጠትና በማረጋገጥ፣ ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ በመስጠትና በማደስ፣ በህግ የተከለከሉ ሰዎች በህገ-ውጥ መንገድ ከአገር እንዳይወጡና ወደ አገር እንዳይግቡ ቁጥጥር በማድረግ፣ ለውጭ አገር ዜጎች በሕግ መሰረት ዜግነት በመስጠት፣ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባን በማካሄድ እና የብሄራዊ መታወቂያን በመስጠት የአገሪቱን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አገለገሎቶቸን የሚሰጥ አገልግሎት መሥሪያ ቤት ነው፡፡
 አገራችን ኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ስፋት ያላት እና ከአጎራባች አገራት ጋር ወደ 6000 ኪ.ሜ. የድንበር ወሰን የምትጋራ ሲሆን ድንበሩ በአብዛኛው ሊባል በሚችል መልኩ ክፍት ወይም የተፈጥሮ ወሰን የሌለው (Porous Border) ነው፡፡ አገልግሎቱ በ18 የድንበር ኬላዎች ምንም መሠረተ ልማት በሌላቸውና ከፍተኛ ሙቀት ባሉባቸው በረሃማ አከባቢዎች የ24 ሰዓታት የድንበር ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይምረጡ