Participate

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ

Portal Admin, modified 2 Years ago.

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ

Youngling Posts: 6 Join Date: 1/22/18 Recent Posts
ሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ ለውጦች ውስጥ እያለፈች ሲሆን፣ ለውጡ ዲሞክራሲን፣ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም እድገት እና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የፖለቲካ ስርዓት ሊያረጋግጥ የሚችል መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተስፋ ቢደረገም በለውጡ ደስተኛ ያልሆኑና የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው የውስጥና የውጪ ሀይሎች ለውጡን ለመቀልበስ  በቅንጅት በርካታ አፍራሽ ተልእኮዎችን እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡  ሌላው ለውጡን እየፈተነው የሚገኘው  በሃገሪቱ  ልሂቃን መካከል በተለያዩ መሰርታዊ ጉዳዮች በተለይም በሀገራዊ መግባባት እጅግ በሚያስፈልግባቸው ጭብጦች ዙርያ ያለው ተቃርኖ ነው። ይህ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳይቀር የሚስተዋለው ሰፊ የሆነ የሀሳብ ልዩነትና አለመግባባት የተረጋጋ እና የሰከነ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት መገንባትን እጅግ አስቸጋሪ የሚያደርገው በመሆኑ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ነው። በልሂቃን መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ፣ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዲሞክራሲ ሽግግር ሂደቱን እጅግ ፈታኝ አድርጎታል። ይህ ቅራኔ እና መዘዙ ከልሂቃን አልፎ በማህበረሰቡ ውስጥ እየሰረፀ ከፍተኛ ምስቅልቅል ማስከተሉ እሙን ነው።
ሀገራት እንዲህ አይነት ፈተና ሲያጋጥማቸው ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት የተለያዩ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን ከነዚህ ዘዴዎች መካከል አንዱና በአሁኑ ወቅት በብዙ ሀገሮች ተሞክሮ ውጤታማ እየሆነ የመጣው ራዊ ውይይት ነው፡፡ በመሆኑም በሀገራችን እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሀገራዊ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ የታመነበት ሲሆን፣ ይህን ሀገራዊ ምክክር የሚመራ እና የሚያሳልጥ አካል በህግ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ አዋጅ የተዘጋጀ ሲሆን የአዋጁ ማብራሪያ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡

Vote