Participate

ስለ ዕጽዋት ዘር ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

Tigist T, modified 1 Year ago.

ስለ ዕጽዋት ዘር ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

Youngling Posts: 21 Join Date: 3/15/18 Recent Posts
የኢትዮጵያ የዕፅዋት ዘር ዘርፍ የግብርና ምጣኔ ሃብት ዕድገትን፣ የምግብ፣ ስነምግብ እና የመኖ እንዲሁም የደን ውጤቶችን ዋስትና ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ዘላቂ የዕፅዋት ዘር ሥርዓት በመዘርጋት የዝርያ እና ዘር በብዛትና በጥራት ለአምራቾች እንዲቀርብ በማድረግ ሥርዓተ ምህዳር ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ በማስፈለጉ፤
የግልና የመንግሰትን የዕፅዋት ዘር ኩባንያዎች በማሳተፍ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ ለምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ሥርፀት፣ ለምርትና ምርታማነት ዕድገትና ለምርት ጥራት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በላቀ ደረጃ ማሳደግ በማስፈለጉ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

Vote