-
የተከበሩ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ የተከበሩ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 54/1/ መሠረት ሁሉ አቀፍ ነፃ ቀጥተኛ ትክክለኛ በሆነና ድምፅ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ በሚመረጡ አባላት የሚመሠረት ተቋም እና የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው፡፡ ምክር ቤቱ ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጠው የሥልጣን ክልል ህጐችን የማውጣት የህግ አስፈጻሚው አካል የሚዋዋላቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶች የማጽደቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የአስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር የፌዴራል መንግሥት ፍርድ ቤት ዳኞችን፣የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፣ የኮሚሽነሮችን የዋናው ኦዲተርን እንዲሁም የሌሎች ሹመታቸው በምክር ቤቱ መጽደቅ ያለበትን ባለሥልጣኖች ሹመት የማጽደቅ ሥራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ም/ቤቱ

የአስፈጻሚውን አካል የሥራ እንቅስቃሴ ከመከታተልና ከመቆጣጠር አኳያ መሠረት አድርጐ የተነሳው የ5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅድ ሲሆን በእቅዱ በግልፅ እንደተቀመጠው አጠቃላይ እንቅስቃሴው ግልጽ፣አሣታፊና ተደራሽ እንዲሆን በላቀ ደረጃ መፈጸም ከሚቻልባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ የምከር ቤቱን ድረ-ገጽ በዘመናዊ መንገድ በመጠቀም መሆኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ በሕዝቡና በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያደርጋቸውን የሥራ እንቅስቃሴዎች የሚመለከቱና ተያያዥ መረጃዎችን ለሕዝባችንና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ማድረስ ይቻል ዘንድ ይህን ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ ድረ-ገጽ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ አውሏል፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚዎች ከምክር ቤቱ ጋር የተያያዙ ወቅታዊና ነባር መረጃዎችን ማግኘት፣ በምክር ቤታዊ የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላችሁን አስተያየት መስጠትና ምክር ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥባቸው የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በማንሳት መሣተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽኩ ምክር ቤቱ ተደራሽነቱን አሣታፊነቱንና የሕዝብ አገልጋይነቱን ለማስፋት ተግቶ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጣለሁ፡፡


 

ቋሚ ኮሚቴ ቋሚ ኮሚቴ

የግብርና ምርምሩ ድግግሞሽን ያስወገደና የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት ሊቀይር የሚችል መሆን ይገባዋል ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስገነዘበ፣

  ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ስር ካሉት 17 የፌደራል ግብርና ምርምር ማዕከላት መካከል የሆሎታ...

ዝርዝር ዜና » share


Web Content Image
የክበበ ፀሐይ ህፃናት ማሳደጊያ ተቋም የክሊኒክ ግንባታ መጓተት በህጻናቱ የህክምናና የላብራቶሪ አገልግሎት ላይ ተጽእኖ አሳድሯል ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፣ ቋሚ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ስር በሚገኘው የክበበ ፀሐይ...

ዝርዝር ዜና » share


በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ ሴቶችን ለማብቃት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ

  ቋሚ ኮሚቴው ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም የአስፈፃሚ አካላትን የሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት እቅድ አፈፃፀም በተመለከተ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ...

ዝርዝር ዜና » share


መደበኛ መደበኛ

Web Content Image
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባለፉት 9 ወራት 165 የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ መቻሉን ገለፀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የተቋሙን የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ኮሚቴው ባቀረቡበት ወቅት የገጠርና ከተማ መሬት...

ዝርዝር ዜና » share


Web Content Image
    ፍትሀዊና የንግድ ስርዓት ለመዘርጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ የንግድ ሚኒስትሩ  አቶ ያዕቆብ ያላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ባቀረቡት የ9 ወራት የስራ አፈጻፀም ሪፖርት ፍትሀዊ ውድድርን መሰረት ያደረገ...

ዝርዝር ዜና » share


Web Content Image
በዘጠና አራት መስሪያ ቤቶች እና በአስራ አንድ ቅርንጫፎች ላይ ብቻ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ አግኝቻለሁ ሲ ል የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን የ2008 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ...

ዝርዝር ዜና » share


አፈጉባኤ አፈጉባኤ

ኢትዮጵያ ስደትን ለመቀነስ፤ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ብቻም ሳይሆን ለዜጎቿ ዘላቂ ልማት መረጋገጥ ከአዉሮፓ ህብረት ጋር በቅርበት መስራት ትፈልጋለች ሲሉ አፈ - ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ገለፁ

  አፈ- ጉባኤው የአዉሮፓ ህብረት ፓርላማ የሶሻልስትና ዴሞክራት ተራማጅ...

ዝርዝር ዜና » share


Web Content Image
ምክር ቤቱ በአገሪቱ የተጀመረውን መልካም አስተዳደር የማስፈን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱን አጠናክሮ እንደሚ ቀጥል አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ አረጋገጡ፣ አፈ-ጉባኤው የምክር ቤቱን የ2008 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ...

ዝርዝር ዜና » share


Web Content Image
አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በስዊድን ፓርላማ   የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር በኬኔዝ  ጂ. ፎርስሉንድ የሚመራ የልኡካን ቡድንን ተቀብሎ አነጋገረ። አፈ-ጉባኤዉ ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ጋር የልኡካን ቡድኑን በመቀበል በተለያዩ ርእሰ-ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል። ኢትዮጵያ አረንጓዴ...

ዝርዝር ዜና » share