የሕይወት ታሪክ

ስሜ አቶ አገኘሁ ወርቁ እባላለሁ። ከአባቴ ከአቶ ወርቁ ቦሪያብ ከእናቴ ከወ/ሮ ቡዙነሽ ፉቹ ግንቦት 29 በ1979 ዓ.ም በሸኮ ወረዳ ተወለድኩ። ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በሸኮ ወረዳ ሸኮ ከተማ አንደኛና ሁለተኛ ትምህርት ቤት አጠናቀኩኝ። በመቀጠል በመምህርነት ኮሌጅ በመግባትበድፕሎማ በመምህርነት ተመርቄ በተለያዩ አከባቢዎች በማስተማር ስራ ቆይቻለሁ። በሸኮ ወረዳ በቋንቋ፣ባህል ቱሪዝም በተሰጠኝ ሹመት ያገለገልኩየሸኮኛ ቋንቋ ማስተማሪያ እና መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቻለሁ። በተጨማሪ እንግልዘኛ-ሸኮ-አማረኛ ድክሽነሪ በመፃፍ ለንባብ እንድበቃ አድርጊያለሁ። በ2001 G.C ትዳር መስርቶ 6 ልጆች በማፍራት እስካሁን አብረን ከባለቤቴ ጋር እየኖርን እንገኛለን። ከድፕሎማ መምህርነት የመጀመሪያ ድግሪ በትምህርት አመራርና አስተዳደር የተማርኩት ሲሆን የሁለተኛ ድግሪ በፕሮጀክት ማናጅመንት ፕላንግ ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ መመረቅ ችያለሁ። የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ በመሾም ህዝብን በማገልገል በተጨማሪ የሸኮ ወረዳ ምክር ቤት አባል ሁኜ አገልግያለሁ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሄረሰብምክር ቤት አበል ሁኜ በታማኝነት ያገለገልኩ ሲሆን በምክር ቤቱየህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመሆን አገልግያለሁ። በ2016 ዓ.ም የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ በመሆን እያገለገልኩበ7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የሸኮ ልዩ ምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በመወከል ተወዳድሬ አሸንፌ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆንኩ። ከዚህ በሀላ ያለውን እግዚአብሔር ያውቃል።