የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

President

የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ

መልዕክት

"

በዴሞክራሲ ማሕበረሰብ ፓርላማ የፖለቲካ ተሳትፎ መገላጫ ነው፡፡ የፓርላማ ዴሞክራሲ ሥርዓት በአንድ አገር መጠናከር ለዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነትና ለማህበራዊ ፍትሕ መረጋገጥ ወሳኝ ሲሆን አስፈፃሚው የመንግሥት አካል በተጠያቂነትና በግልፅነት ስራውን እንዲያከናወን ያስችላል፡፡ በሀገራችን የፓርላማ ዴሞክራሲ ስርዓት መተግበር ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን አምስት የምክር ቤት ዘመናት አልፈው እነሆ አሁን በ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው፡፡ በየአምስት ዓመቱ በሚካሄድ ብሔራዊ ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ አግኝተው በሚመረጡ አባላት ይመሰረታል፡፡ አባላቱም ሁሉ አቀፍ፣ ነፃ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡አባላቱ ተጠሪነታቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ ተገዥነታቸውም ለሕገ መንግሥቱ፣ ለሕዝቡና ለሕሊናቸው ነው፡፡ ምክር ቤቱ በሕግ አወጣጥ፣ በክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም በውክልና ሥራዎች የሚያከናውናቸው ተግባራት እና የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ወሳኝ መሆናቸው ይታወቃል፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕይወት ላይ በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸው ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ ለሀገር ሠላም፣ ለዜጎች ማህበራዊ ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ ናቸው ተብለው በታመኑ ጉዳዮች ላይ በሕግ አወጣጥ ሂደት፣ በክትትልና ቁጥጥር እና በውክልና ተግባራት ተገቢውን ምርመራ በማካሂድ በርካታ ሀገራዊ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡ ለሀገራዊ እቅዶች፣ፕሮግራሞች፣ፖሊሲዎችና ፕሮጀክቶች መፈፀም ፤ የመንግሥትና ሕዝብ ሃብትና ንብረት ለታለመለት ዓላማ ውለው የሕዝብ የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል የመንግሥት ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ምክር ቤቱ ጠንከራ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል፡፡ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ምክር ቤቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን የተቋማት ምላሽም እያደገና እየተሻሻለ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡ በፓርላማ ዲፕሎማሲው ዘርፍ የሀገራችንን ባሕልና እውነተኛ ገፅታ ለማስተዋወቅና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (ንግድና ኢንቨስትመንት) ከመደገፍ ረገድ አበረታች ውጤቶች ለማስመዝገብ የሁለትዮሽና በብዙኽዮሽ መድረኮችን በአግባቡ ለመጠቀም ጥረት ተደርጓል፤ በቀጣይም የፓርላማ ዲፕሎማሲን እንደ አንድ የውጭ ፖሊሲ መሳሪያ በስፋትና በተጠናከረ አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ ምክር ቤቱ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ፈጥነው ተጠናቀው ለህብረተሰቡ የልማት አገልግሎት እንዲሰጡ፣ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣በሥራ ፈጠራና ድህነት ቅነሳ፣ ለሕግ የበላይነትና ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ ምክር ቤቱ በቀጣይ ጊዜያት በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡ ያሉብንን የፖለቲካ ልዩነቶች በንግግር፣ በምክክርና በውይይት ለመፍታት ምክር ቤቱ የአቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ለኮሚሽኑ ተልዕኮ መሳካት ሁላችንም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራዊ የፍቅር ስሜት የበኩላችን ድርሻ ልንወጣ ይገባል፡፡ የአንድነታችን ተምሳሌትና የአብሮነታችን ማሳያ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድባችን በመጠናቀቅ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን የዜጎችን ማህበራዊ ኢኮኖሚ ልማት የሚያፋጥኑ በርካታ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ሥለሆነም ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ከዳር ለማድረስና ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሠላም፣ ለአብሮነታችን መጎልበትና ለብሔራዊ መግባባት አብረን እንድንቆምና ሁላችንም የየራሳችንን አበርክቶ እንድንወጣ በዚህ አጋጣሚ መልዕክት አስተላልፋለሁ፡፡ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የአብሮነት፣ የመግባባት፣ የልማት እና ብዙ ተስፋዎች የምናይበት ዘመን እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡ አመሠግናለሁ!

"ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን" የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ"

"ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን" የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ"

---------------------

(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 16 2018 .ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው፣ ይህ ጉባዔ ለነገዋ ጠንካራ ኢትዮጵያ መሠረት የተጣለበት እና የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የተቀረጸበት ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ የምክክር ሂደት ዋና ዓላማ በሀገራችን ለረጅም ጊዜያት የግጭት መነሻ የሆኑ መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በውይይት መፍታት መሆኑን ያነሡት አቶ ታገሰ፣ ምክክሩ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አካታች እና አጠቃላይ ሀገራዊ መድረክ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።

የምክክር ሂደቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት ራሱን የቻለ እና ገለልተኛ የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካይነት በሕጋዊ ሥርዓት መመራቱን አፈ-ጉባኤው አስታውሰዋል።

ኮሚሽኑ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ በመውረድ አርብቶ አደሮችን፣ አርሶ አደሮችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪክ ማኅበራትን እና ዳያስፖራውን ያካተተ ሰፊ ሥራ ማከናወኑ የምክክሩን ተአማኒነት እና ሕዝባዊ ቅቡልነት ማረጋገጡን አብራርተዋል።

ከሕዝብ እና ከባለድርሻ አካላት በተሰበሰቡ አጀንዳዎች መሠረት ተለይተው በቀረቡ ስምንት ዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከመላው ሀገራችን የተውጣጡ 4,000 በላይ ተሳታፊዎች በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሰፊ ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በዚህም የኃይል እና የጦርነት ፖለቲካን በማስቀረት ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት እንደሚቻል ማሳየት መቻሉን አፈ-ጉባኤው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጉባዔው በስኬት ሲጠናቀቅ ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሔ የሚሆኑ በርካታ ዐበይት ምክረ ሐሳቦች መፍለቃቸውን የጠቆሙት አቶ ታገሰ ጫፎ፣ እነዚህ ምክረ ሐሳቦች ለቀጣይ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ ለሕገ-መንግሥታዊ እና ተቋማዊ ለውጦች፣ እንዲሁም ለዘላቂ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የምክክሩ ዋነኛ ግብ የትናንት ታሪካዊ ስብራቶችን በማከም ለቀጣዩ ትውልድ ሰላሟ የተጠበቀ እና ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር ማስረከብ በመሆኑ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፖለቲካ ኃይሎች እና የመንግሥት አካላት ከምክክሩ የተገኙ ውጤቶችን በባለቤትነት በመጠበቅ ወደ ተግባር እንዲተረጉሟቸው አፈ-ጉባኤው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም በራሳቸው እና በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

See less

 

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ መልዕክት

"በኢትየጰያ አንፃራዊ ሰላም ተረጋግጧል" ----- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

"በኢትየጰያ አንፃራዊ ሰላም ተረጋግጧል" ----- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (/)

-------------

(ዜናፓርላማ) ሰኔ 30 2018 .ም፤ በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም መረጋገጡን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይንን የገለጹት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው 30 መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመንግስትን 2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልልቶ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

የምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናትና የተጀመረውን አገራዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ መንግስት ምን የመፍትሔ አማራጭ አስቀምጧል በሚል ጥያቄ አንሰተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (/ ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት በተደረገው ሁለንተናዊ ጥረት አሁን ላይ መሻሻል እየታየ መሆኑን ገልጸው፤ ለአብነትም የብሔር እና የእርስ በርስ ግጭቶች መቀነሳቸውን አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር እና ሰላሟን ለማጽናት በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በታሪካዊ ጠላቶች ትዕዛዝ ሰጭነት የታጠቁ ሀይሎች እዚህም እዚያም ዓላማ የሌለው ግጭት ቢፈጥሩም የማይሳካላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የመንግስት እና የሀዝቡ ትስስር እያደገ በመጣ ቁጥር የኢትዮጵያ ተግዳሮቶች እየቀነሱ ይሄዳሉ፤ ይበልጥ ሰላምና መረጋጋት ይፈጠራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የታጠቁ ሀይሎች የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ የሚሰራው ስራ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያመጣ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ጊዜያዊ ክልላዊ መንግስት ከማቋቋም ባሻገር ዘርፈ-ብዙ ተግባራት የተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል ሀይል የተገነባ እንደሆነ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያውያን ለውጭ ጥቃት የማይንበረከኩ እንደሆኑ ከታሪካቸው መረዳት አንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ አትወድቅም፤ የወደቁትንም ታነሳለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ የብልጽግና ራዕይና ተልዕኮ ያልገባቸውን አካላት በማንቃት ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው እድገት እንዲተጉ መንግስት በትኩረት አንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

(በተስፋሁን ዋልተንጉስ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

 

 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር የፌዴራል መንግሥትን የ2019 በጀት 2.3 ትሪሊዮን ብር አድርጎ አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር የፌዴራል መንግሥትን 2019 በጀት 2.3 ትሪሊዮን ብር አድርጎ አፀደቀ

-----------------------

(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 30 2018 .ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 30 መደበኛ ስብሰባው 2019 በጀትን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ 2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ የቀረበውን 2.339 ትሪሊዮን ብር በጀት በአዋጅ ቁጥር 1437/2018 አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የውሳኔ ሃሳብ እና ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ከተያዘው አጠቃላይ በጀት ውስጥ 1.49 ትሪሊዮን ብሩ ከታክስ ገቢ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ቀሪው 93.7 ቢሊዮን ብር ከልማት አጋሮች በሚገኝ ብድርና ድጋፍ እንዲሁም 320 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ በሚገኝ ብድር የሚሸፈን መሆኑን ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡

አጠቃላይ የበጀት ጉድለቱ ከጠቅላላው የሀገራዊ ምርት (GDP) ያለው ድርሻ 1.4 በመቶ ብቻ መሆኑ ማክሮ ኢኮኖሚን ለማረጋጋት የተያዘውን የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑም የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ድልድሉ 30 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ ለትምህርት፣ ለመንገድ፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኃይል አቅርቦት ማስፋፊያ እና ለከተማ ልማት የተመደበ ሲሆን፣ ለክልሎች የበጀት ድጋፍ 187.3 ቢሊዮን ብር ወይም 15.1 በመቶ ተመድቧል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 28.4 ቢሊዮን ብር ወይም 17.8 በመቶ ጭማሪ እንደሚያሳይ ተመላክቷ።

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የሚመደብላቸውን በጀት በላቀ ውጤታማነት እና ለታለመለት ዓላማ በማዋል በኃላፊነት ስሜት ሊፈጽሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሚመደበውን በጀት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አይይዘው አስገንዝበዋል፡፡

(በመኩሪያ ፈንታ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

 

የፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር አዋጅ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ

የፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር አዋጅ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ

*********************

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 15 መደበኛ ስብሰባ፣ የስፖርት ዘርፍ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበትን የፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

አዲሱ አዋጅ ቁጥር 1413/2018 በስፖርቱ ዘርፍ አካታች፣ ዘመናዊና ግልጽነት ያለው የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ምቹ መደላድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩ የአሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ታላቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

አዋጁ የስፖርት መሠረተ ልማቶችንና ማሰልጠኛ ተቋማትን ከማስፋፋት ባለፈ፣ የስፖርት ግብዓት አምራቾች እንዲበረታቱና ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ያደርጋል።

በተጨማሪም ማህበራዊ ትስስርን በማጎልበት፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማጠናከር እና ስፖርት ነክ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በምክር ቤቱ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ አብራርተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር / ሸዊት ሻንካ በሰጡት ማብራሪያ፣ ስፖርት የኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ እንዲሆን ዘርፉን የያዙ ማነቆዎችን በአሰራርና በስርዓት መፍታት የግድ እንደሚል ጠቁመዋል።

አዋጁ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ በማድረግ ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም የአዋጁን አስፈላጊነት በማመንና አፈጻጸሙ ላይ ትኩረት እንዲደረግ በማሳሰብ አዋጁን በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

በጾታ
በፖለቲካ ፓርቲ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሥልጣንና ተግባር:-

  • ሕግ ማውጣት፣
  • የፌደራል መንግስት በጀትን መርምሮ ማፅደቅ፣
  • መንግስታዊ አካላትን መከታተል፤ መቆጣጠር እና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝም እርምጃ መውሰድ፣
  • የራሱን የተለያዩ ኮሚቴዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ክፍሎችን ማቋቋምና ማደራጀት፣
  • በራሱ የሚሰየሙ፣ የሚሾሙ እና የሚመረጡ የመንግስት ባለስልጣናትን መሰየም፣መሾም፣ማፅደቅና መምረጥ፣
  • አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር እንዲገናኙ  ማመቻቸት።

Image

የጽ/ቤቱ ተልዕኮ፣ ረዕይ እና ዕሴቶች

ተልዕኮ

ጽ/ቤቱ የም/ቤቱ አባላትና አካላት ለሚያከናውኗቸው የሕግ አወጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር፣ የውክልና እንዲሁም የፓርላማ ዲፕሎማሲ ተግባራት የማማከር፣ የጥናትና ምርምር አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጠት እና የመረጃ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ነው።

ርዕይ

በ2022 ነፃ፣ ገለልተኛና ጥራት ያለው ሙያዊና አስተዳዳራዊ አገልግሎት የሚሰጥ ጽ/ቤት መሆን፣

የተቋሙ ዕሴቶች

  • ለጋራ ስኬት መቆም፣
  • ቀጣይነት ያለው ለውጥ፣
  • ግልፅነትና ተጠያቂነት፣
  • መከባበርና መተባበር፣
  • ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት፣
  • ታማኝነትና ቅንነት፣
  • ውሳኔ ሰጭነት እና
  • ብዙኃነት ናቸው፡፡