ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ካሣሁን ደለነ ደያሣ ከእናታቸው ወ/ሮ ስንታዬሁ ሜትሶ እና ከአባታቸው አቶ ደለነ ደያሣ ጥር 29/1985 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ድል ፋና ቀበሌ ተወልደዋል። በኮንሶ ዞን ካራት ሙሉ 1ኛ ደረጃ የተጀመረው ትምህርታቸው በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ወርጅሜይሳ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና በኋላም በላስካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና በማጠናቀቅ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል። የከፍተኛ ትምህርት ቆይታቸው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና በሌሎች የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተከታትለዋል።
ዶ/ር ካሳሁን በወጣትነታቸው የሙያ ሃላፊነታቸውን እስከ ዓለምአቀፍ የምርምር ተቋማት ድረስ ያገለገሉ እጅግ ታታሪ እና ቆራጥ ሰው ናቸው። በሙያቸው በሳይንሱ ዓለም በሀገራችን ትኩረት ያልተሰጣቸውን የአዞ በሽታዎችን በማጥናት በመመራመር እና ግኝታቸውን በማሳተም ይታወቃሉ። ከአርባምንጭ እስከ ዓለምአቀፉ የአዞ ተመራማሪዎች ቡድን አባል በመሆን ለዘርፉ ሳይንስ ላቅ ያለ አስተዋፅዖ አበርክተዋል። የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ካሳሁን ለአንድ ጤና (One Health) ትኩረት በመስጠታቸው ይታወቃሉ። የሚባክን ጊዜ የሌላቸው ባለሙያው ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማቅናት በ2011 የሂሳብ መዝገብ አያያዝ (Accounting and Finance) በድግሪ አጠናቅቀዋል።
በፓን አፍሪካ ንቅናቄ Global Pan Africanism Network-GPAN የሚባል ህብረት ከጓደኞቻቸው ጋር ከማቀንቀን ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የወጣቶች ዕጩ ቋሚ መልዕክተኛም ነበሩ። በኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት መስራች አባልና የኦዲትና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊም ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። የአፍሪካ ወጣት እንደራሴዎች መረብ African Young Parliamentarians Network አባል በመሆንም እያገለገሉ ይገኛሉ።
ከሁለተኛ ደረጃ የተማሪዎች ህብረት ፕረዚዳንትነት የጀመረው የፖለቲካ ልምምዳቸው በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ውስጥ ከአባልነት ጀምረው በህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ በአባልነት: በድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባልነትና ም/ሰብሳቢነት: በኢዜማ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማህበራት መምሪያ ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል። በ6ኛው ዙር የሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ፓርቲያቸውን ወክለው ተወዳድረዋል።
ዘርፈ ብዙ እና ሁለገብ የሆኑት ዶ/ር ካሣሁን ደለነ ከዚህ ቀደም ተቀማጭነታቸውን ካናዳ ላደረጉ The African Industrialization Group Inc./Holding Ltd የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ እና የኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ: Chongqing Fangtong animal Pharmaceutical manufacturing factory በተሰኘ የቻይና ድርጅት ውስጥ Country Representative በሙሆን እና በሌሎች የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጅቶች ውስጥ በተለያየ መርህ: ሙያ እና ሹመት ሀገራቸውን አገልግለዋል።
በአሁን ሰዓት የ6 የልማት ማህበሮች አባል ሲሆኑ ከ10 በላይ የሀገር ውስጥና የዓለምአቀፍ የሙያና የምሁራን ማህበር አባል ናቸው።