የሕይወት ታሪክ

እኔ አቶ ባዜን ሽባባው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ ደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ቀበሌ ከአባቴ ከአቶ ሽባባው ዓለማየሁ እና ከእናቴ ከወይዘሮ ተቋም ጓዴ ሕዳር 12/1974 ዓ.ም ተወለድኩ። የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ከጎርጎራ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትያለሁ። የመጀመሪያ ዲግሪየን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጆግራፊ ማይነር ታሪክ በደመኛው ፕሮግራም CGPA 3.68 በማምጣት ተመርቂያለሁ። እንዲሁም ማስትሬት ዲግሪየን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በፌዴራሊዝም እና ሎካል ገቨርንመንት ስተዲስ CGPA 3.57 በማምጣት ተመርቂያለሁ። በተማርኩት ሙያ በላቀ ዕውቀት፣በክህሎትና በአዎንታዊ አመለካከት በመቃኘት እንዲሁም በከፍተኛ ተነሣሽነት ፣ በቁርጠኝነት፣በብቃት፣በተግባቦት ክህሎት፣ከቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ በቅንነት በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ሕዝብን አገልግያለሁ፤ እያገለገልኩ ነው። በግንቦት 23/2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ብሔራዊ ምርጫ ፓርቲዬን ብልፅግናን ወክዬ በደንቢያ ቁጥር 2 የምርጫ ክልል ዕጩ ሆኜ በመቅረብ፤በምርጫ ውድድሩ አሸንፌ የኢፊድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኛለሁ።