ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ገነነ ገዛኸኝ (ዶ/ር) በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክፍሌ ሀገር ጋርዱላ አውራጃ ዋሌሳ ቀበሌ ከአባቴ ገዛኸኘ ኖቦ እና እናቴ ታየች ደበላ በ1979 የተወለድኩ ሲሆን ዕድሜዬ ለትምህርት ስደርስ በ1987 ዓም ጊዶሌ አንደኛና መለስተኛ ትምህርት ቤት በመግባት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል እዛው ተምሬ በ1994 የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በከፍተኛ ውጤት በማለፍ ወደ ጊዶሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1995 በመግባት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተከታትዬ በ1998 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ክፍተኛ ውጤት በማምጣቴ በ1999 ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገብቼ በሐምሌ 2001 ዓ/ም ባበዮቴክኖሎጂ የመጀመያ ዲግሪ በከፍተኛ ውጤት ተመረቀኩ፡፡
ከትምህርት ዓለም በኋላ በጥር 2002 በደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አረካ ማዕከል ጀማሪ ተመራማሪ በመሆን የሥራውን ዓለም ተቀላቀልኩ፡፡ ከ2002 እስከ ዛሬ ደርስ በተመራማሪነት፣ በምርምር አስተባባሪነት በተለያዩ የተመራመሪ ደረጃዎች እስከ ከፍተኛ ደረጃ እና የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተርነት መድረስ ችያለው፡፡ በነበረኝ 16 ዓመት ከ8 ወራት የሥራ ቆይታ መሐል ተቋሙ በሰጠኝ የትምህርት እድሎች በሀሮማያ የሁተኛ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲዎች ተከታትያለው በበነበረኝ የሥራና የትምህርት ቆይታ በግልና በቡድን የተሰሩ የምርምር ግኝቶች እና የህትመት ውጤቶች የክልሉን እና ሀገራችንን የግብርና ምርምርና ልማት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው ብዙ ማሳያዎች ምስክሮች ናቸው፡፡
ከመደበኛ የመንግስት ሥራ ጎን ለጎን በደራሼ አካባቢ ማህበረሰብ መካከል የሚፈጠሩ ግኝቶችን እና የልማት ፍላጎቶችን ለመፍታት የምሁራን ህብረትን ለመመስረት ሀሳብ ከማመንጨትና ሰብሳቢ በመሆን እያገለገልኩ እገኛለው፡፡