የሕይወት ታሪክ

እኔ ልጃለም አየለ ረጋሳ ከአባቴ መ/ር አየለ ረጋሳ እና ከእናቴ መ/ት ፍቃዴ ብሩ በቀድሞ ኢሉባቦር ዞን ገቺ ወረዳ በ1976 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በገቺ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በበደሌ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ በ1994 ዓ.ም አጠናቅቅያለዉ፡፡ በ 1996 ዓ.ም ከ ጂማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኬሚስትሪ ትምህርት ዲፕሎማ፣ በ2001 ዓ.ም ከጂማ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ትምህርት የመጀመሪ ዲግሪ፣ በ2004 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ በኢኖርጋኒክ ኬሚሰትሪ የማስትሪት ዲግሪ እንዲሁም በ2009 ዓ.ም ከ አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ በኢኖርጋኒክ ኬሚስትሪ የዶክትሬት ዲግሪዬን አግንቻለዉ፡፡ በተጨማሪም በ2007 ዓ.ም ከ አዉቶኖማ የኒቨርሲቲ ኦፍ ማድሪድ ስፔን ሀገር የሦስት ወር የትምህርት ላይ ስልጠና፤ በ2011 ዓ.ም ከተባበሩት አረብ ኤምሬተስ የ አምስት ቀናት የፕሮጂክት አስተዳደር ስልጠና፣ በ2015 ዓ.ም ከጣሊያን ሀገር ቴርስቴ ከተማ የአምስት ቀናት የሳይንስ ዲፕሎማሲ ስልጠና አንዲሁም በ2018 ዓ.ም ከቻይና ሀገር ዉሃን ከተማ በ‘’Seminar on International Cooperation for BeiDou Navigation Satellite System Application Going global for African Countries’’ የ አስራ አምስት ቃናት ስልጠናን በመከታተል የምስክር ወረቀት አግንቻለዉ፡፡ በተለያዩ አለመ አቀፍ ጥናትና ምርምሮች ላይ በመሳተፍም ሰባተት የጥናትና ምርምር ዉጥ  የስራ ልምዴን በተመለከ፣ ከ 1997 እስክ 1999 ዓ.ም በ ኢሉባቦር ዞን ያዮ ወረዳ የያዮ አይዳትያ ሁለተኛና መሰናዶ ት/ቤት የኬሚሰትሪ መምህር፣ ከ 2004 እስከ 2005 በ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኬሚስትሪ ት/ክፍል በ ሌክቸረርነትና ተመራማሪነት አንዲሁም በተለያዩ ሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የደህረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን የመመረቂያ ጽሁፍ ማማከርና መፈተን ያገለገልኩ ሲሆን ከ 2009 ዓ.ም እስካሁን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግስት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በምክትል ኃላፊነት በሹመት በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡