የሕይወት ታሪክ

ስሜ ፈቲያ አልይ መሀመድ ፣ የተወለድኩበት ኦሮሚያ ክልል ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ፣ በሸነን ዱጎ (መሰላ) ወረዳ ሲሆን፣ እድሜ ለትምህርት ሲደርስ በመሰላ መለስተኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርቴን የተከታተልኩ ሲሆን፣ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል በጭሮ ከተማ ጨርጨር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህትቴን በበቂ ሁኔታና በስኬት አጠናቅቄለሁ፡፡ ከዚህም በመቀጠል ዲፕሎማ በኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ በማጠናቀቅ ፣1ኛ እና 2ኛ ዲግሪ በርፍትቫሊ ዩኑቨርሲቲ ኮሌጅ ያጠናቀቅኩ ሲሆን በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1999 ዓ/ም እስከ አሁን 2018 ዓ/ም ድረስ ከባለሙያነት እስከ አመራርነት ከሕዝብና ከመንግስት የተሰጠኝ ኃላፊነት በሰራሁባቸው ሥራዎች በሙሉ በብቃት፣በታማኝነት፣ እንድሁም በትጋት ሲወጣ ቆያቻለሁ፡፡