ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኦሮሚያ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ኬይሩ ሐጂገቢ ሐዪ ይባላል ። በ1982 ዓ.ም. በኢታያ ከተማ፣ ሄጦሳ ወረዳ ተወለድኩ። አባቴ አቶ ሐጂጋቢ ሐዪ ሲሆኑ፣ እናቴ ደግሞ ወይዘሮ ጀሚላ ቱማ ናቸው።
የትምህርት እድሜዬ ሲደርስ፣ በኢታያ አንደኛና መለስተኛ ትምህርት ቤት ትምህርቴን ጀመርኩ። ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በዚያ ተምሬያለሁ። ከዚያም 9ኛ እና 10ኛ ክፍልን በመጋላ ደራ ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በዲፕሎማ ተምሬያለሁ። በተጨማሪም በቢዝነስ ማኔጅመንት የዲግሪ ትምህርቴን አጠናቅቄያለሁ።
ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ በኢታያ ከተማ በመጠጥ ውሃና በፈሳሽ አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ማኅበረሰቤን እያገለገልኩ ነው። በአሁኑ ጊዜ የፋይናንስ ዳይሬክተር ሆኜ በማገልገል ለማኅበረሰቤ ልማትና አገልግሎት የበኩሌን እያበረከትኩ እገኛለሁ።
በ አሁን ሰዓት በ7ኛው የኢትዮጵያ አገራዊ ምርጫ ወረዳዬን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ በመታጨት የፓርላማ አባል በመሆን ታጪቼ በመመረጥ ህዝቤን ለማገልገል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ።
የትዳር ሁኔታ ባለትዳረ እና የሶስት ልጆች እናት ነኝ