የሕይወት ታሪክ

ግለ-ታሪክ እኔ እንድሪስ ወርቁ ጉሳ እባላለሁ። ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲፕሎማ በ2008 እና የመጀመሪያ ዲግሪ 2015 ዓ.ም የትምህርት ደረጃ በትምህርት መስክ ያለኝ ስሆን በመካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (7-12) ክፍል ደረጃዎች በማስተማር 10 ዓመታት የስራ ልምድ አለኝ። በእነዚህ ዓመታት ደንበኞቼ -ተማሪዎች የትምህርቱን ይዘት በቀላሉና በግልጽ እንድረዱና ቀጣይ ጥናት ጊዜያቸው ላይ ሳይቸገሩ እንድማሩ መርዳት መቻለ ትልቁ ስከቴ ነው። አዳዲስ ሁኔታዎችን በቀላሉ የመልመድና የተግባቦት ክህሎቴ ከፍተኛ ነው። ከመምህርነት ስራዬ ጎን ለጎን፣ ለማኅበራዊ ፍትህ እጦት ካለኝ ትልቅ ቁጭት የተነሳ፣ በ7ኛው ጠቅላላ ኢትዮጵያ ምርጫ በኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) የሚኖርበት አካባቢ ህዝብን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድሬ የተመረጥኩና ያሸነፍኩ ስሆን ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦይዳ ህዝቦች ተወካይ እና የፓርላማ አባል ሆኘ የመረጠኝን ህዝብ በታማኝነት መወከል ደግሞም ሀገረን ኢትዮጵያንም በቅንነት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ።