የሕይወት ታሪክ

ሰሜ ዶ/ር ሩቅያ አልይ ካዎ እባላለዉ። ከአባቴ አልይ ካዎ እና ከእናቴ ከጂዳ ሂኮ በ1981 በገደብ ሀሳሳ ወረዳ፣ ጥጆ ወቄንጠራ ቀበሌ ተወለድኩ። እድሜዬ ለትምህርት ስደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በ1987 ዓ.ም በሀሳሳ ቡርቂቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀመርኩ። በሀሳሳ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል (መሰናዶ) እዚያው ተከታትዬ (በ1998 ዓ.ም.) አጠናቀኩ። የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት አስመዘገቤ በ1999 1ኛ ዲግሪ በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ በ2003 2ኛ ዲግሪ በአድስ አበበ ዩኒቨርሲቲ እና በ2004 በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት ተመድቤ አራት አመት ከሰራሁ ቦሃላ ወደ አድስ አበበ በመመለስ በ2012 ፒ.ኤችዲ በአድስ አበበ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀኩ። በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ ከመመር መስተማር ስራ በተጨማሪ የመህበረሰብ አገልግሎት ስራ ስሰራ ቆይቻለሁ፣ ሥራዬ በተለይም በጨረር መለኪያ፣ በአካባቢ ራዲዮአክቲቪቲ፣ በተፈጥሯዊ ራዲዮኑክላይዶች፣ በጋማ-ሬይ ስፔክትሮሜትሪ እና በጨረር ደህንነት ላይ ያተኮረ ስራዎችን ሰርቻለሁ። በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ጨረር እና ራዲዮአክቲቪቲ የሚያጠነጥኑ ሦስት ሳይንሳዊ ጽሑፎችን አሳትምያለሁ፣ በአፉን አኦሮሞ አራት መጻሕፍትንም ጽፍያለሁ። በ2014 የምክር ቤት አባል በመሆን እስከ 2018 አገለገልኩ። በፓርላማ ውስጥ ያሉ ሴቶች ቡድን (Women in Parliament Caucus) የአቅም ግንባታ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የከተማ መሠረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባል ✓ የሰው ኃይል እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ✓ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ✓ የአራተኛው የፓርላማ የምርምር ጉባኤ ቡድን አባል ✓ በኢትዮጵያ የሙሁራን ሚና በሀገር ግንባታ ላይ በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ አወያይ ✓ በ"ኢትዮጵያ ሴቶች በኒውክሌር ዘርፍ" (Ethiopia Women in Nuclear) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ✓ በኢንተርፕረነሮች ልማት ተቋም አሰልጣኝ የ7ኛ ዙር የምርጫ-ቅድመ ዝግጅት ጥናት ቡድን ሰብሳቢ በመሆን ሰርቻለሁ። አሁንም የ7ኛ ዙር የምክር ቤት አባል በመሆን ተመሪጫለሁ።