ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ሰናይ አኩዎር ኡቻላ ከአባቴ አቶ አኩዎር ኳችኳር እና ከእናቴ ወ/ሮ ኝግዎ ዉዶ አጁሉ በ1970 ዓ.ም በኢሉባቦር ክ/ሀገር ጋምቤላ አዉራጃ ጋምቤላ ወረዳ ፒሞሊ ቀበሌ ውስጥ ተወለድኩኝ። ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ 1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በአቦል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ7ኛ እና 8ኛ ክፍልን በጋምቤላ ከፍ/ሁለተኛ ደረጃ ትምህት ቤት፣ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል በኦፔኖ መካከለኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም 11ኛ እና 12ኛ ትምህርት በጋምቤላ ከፍ/ሁ/ት/ቤት የቀለም ትምህርቴን አጠናቀቁኝ። በመቀጠሎ ወደ ኮተብ መምህራን ትሞህርት ኮሌጅ በ1991 ዓ.ም በመግባትበ1992 ዓ.ም በታሪክ ትምህርት በመምህርነት ሙያ ተመረቁ።
ከዚያ ለሁለት ዓመታት በፒኝውዶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 9ኛ፣ 11ኛ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማስተማር ሳገላገልና በአቦል መካከለኛ ሀለተኛ ት/ቤት በት/ቤት ዳይሬተርነት አገልግያለው።
ሕግን ትመህርት ከአንዳንድ መጽሐፍትና ከሚሰሩ ጓደኞቼ በአገኘው መረጃ ህግን የመማር ፍላጎት ስለአደረብኝ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መግቢያ ፈተና በመፈተን የሕግ ትምህርት በ1995 ጀምሬ በ1998ዓ. ም የመጀመሪያ ዲግሪ አገኘው።
በክልሉ ፍትህ በጠቅላይ ዓቃቤ-ሕግነት ከአገላገልኩ በኃላ በተመሳሳይ ኮሌጅ ለማስተርስ ፕርግራም መግቢያ ፈተና በመፈተን በ2001ዓ. ም ትመህርቱን ጀምሬ በ2002 ዓ.ም በንፅፅር ሕግና መልካም አስተዳደር ትምህርት የማስተርስ ዲግሪ ያዝኩኝ። ከሕግ ማስተርስ ዲግሪ ማግኘት በክልሉ መንግሥት የነበረ ፖለቲካ ፓርቲና የሀገሪቱ መንግሥት ሪፎርም ተከተሎ የብልፅግና ፓርቲ አባል በመሆን በተለያዩ የመንግሥት በአመራርነት ተመድቤ እያገላገልኩ ይገኛለው።
በትዳር ህይወቴ ባለትዳርና የአንድ ወንድና ሦስት ሴት ልጆች አባት ነኝ።