ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ፈትህያ መሐመድ በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ ደደር ወረዳ በሚገኘው አባዬ ቀበሌ ከአባታቸው አቶ መሐመድ አብደላ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዛህራ መሐመድ 1972አም ተወለዱ። እድሚአችዉ ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያና የመሠረታዊ ትምህርታቸውን በድሬዳዋ እና በደደሪ ተከታትለው የ11ኛና 12ኛ ክፍልን በደደሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ።
የሙያ ጉዟቸውን በነርሲንግ ዲፕሎማ በመጀመር፣ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኒካል ረዳትነት ሥራ ጀምረዉ ትምህርታቸውን በመቀጠል ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በነርሲንግ( BSc) ዲግሪአችዉን አጠናቀዉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መምህርነት ተሸጋገሩ። በመቀተል ልዩ ሙያቸውን ለማሳደግ በClinical and Community Mental Health የMSc ዲግሪያቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ 2015 አግኝተዋል።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና (Psychiatry) ክፍል ኃላፊ በመሆን ለሁለት ዓመታት ያህል የአመራር ኃላፊነትን ተወጥተዋል። በመቀጠልም በስኪዞፍሬኒያ የበሽታ ስርጭት አዝማሚያና የሕክምና ሂደት ላይ ያካሄዱትን የዶክትሬት ምርምር በማጠናቀቅ፣ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. (July 2, 2024) በአእምሮ ጤና ዘርፍ PhD ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
ዶ/ር ፈትህያ ከ25 በላይ በሙያዊ ግምገማ ያለፉ (peer-reviewed) ዓለም አቀፍና ሀገር ውስጥ የሳይንስ ጆርናሎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማሳተም በምርምር ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል። የምርምር ትኩረታቸውም አእምሮ ጤና፣ ስኪዞፍሬኒያ፣ የአእምሮ እድገት እክሎች፣ ስነ-ልቦናና ማህበራዊ እንክብካቤ እና ማህበረሰብ ጤናን ያካትታል።
በአሁኑ ወቅት የአእምሮ ጤና ረዳት ፕሮፌሰር፣ መምህር፣ ተመራማሪና የአእምሮ ጤና አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ተማሪዎችንና የጤና ባለሙያዎችን በማስተማርና በማማከር፣ የሚቀጥለውን ትውልድ የጤና ባለሙያዎች በማብቃት እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል በንቃት ይሳተፋሉ።
በአመራር ዘርፍም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ፆታ፣ የኤችአይቪ/ኤድስ፣ የአካታችነትና የልዩ ፍላጎቶች ተባባሪ ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። በተጨማሪም በምስራቅ ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት እክሎች ላይ የተመሰረተ ፕሮጀክትን በመምራት፣ ለተጋላጭና በማህበረሰብ ውስጥ ለተገለሉ ሰዎች የጤናና የማህበራዊ ድጋፍ እንዲደርስ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ፣ የዶ/ር ፈትህያ ሙያዊ ጉዞ ከገጠር ማህበረሰብ የመነጨ የትምህርት ጥረትን በማሳየት፣ ከነርሲንግ ሙያ ወደ ከፍተኛ የአእምሮ ጤና ሙያ፣ ምርምርና አመራር የደረሰ የስኬት ጉዞ ነው። በትምህርት፣ በምርምር፣ በአመራርና በማህበረሰብ አገልግሎት ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሰው ልጅ ክብርን፣ እኩልነትን፣ አካታችነትንና የማህበረሰብ ደህንነትን ያስቀደመ ሙያዊ እሴታቸውን ያንፀባርቃል።