ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኡራጋ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ፍቃዱ ሣተና ይባላል። አባቴ ሣተና ዱቤ ይባላል። እናቴ ያታኔ ቦኔያ ትባላለች። ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ባጠቃላይ ሶስት ልጆች አሉኝ። የተወለድኩት በ1978 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ዳማ ወረዳ ሐዳ ጉራቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነበር። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን በአፈሌ ኮላና በቡሌ የተከታተልኩ ሲሆን፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በቦሬና በዲላ ተከታትያለሁ። የመጀመሪያ ድግሪዬን ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በሶሾሎጂ የተመረኩ ሲሆን ሁለተኛ ድግሪዬን ደግሞ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በከተማ አመራር ተምሬከለሁ። በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት እርከን በኃላፊነት ያገለገልኩ ሲሆን የተወሰነውን ለመጥቀስ ያክል የቦሬ ወረዳ ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የቦሬ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የቦሬ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የቦሬ ወረዳ የሥራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የቦሬ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የጉጂ ዞን ከተማ ልማትና ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የጉጂ ዞን ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ኃለፊ፤ የጉጂ ዞን መንገዶችና ሎጂስቲክስ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ የጉጂ ዞን የሥራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት እና ባሁኑ ጊዜ ደግሞ የአዳማ ከተማ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ኃላፊ ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ።